ዘፀአት 14:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የንጉሡን ልብ ስላደነደነ በድፍረት በመውጣት ላይ የነበሩትን እስራኤላውያንን አሳደዳቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የንጉሡን የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው በልበ ሙሉነት ከግብጽ የሚወጡትን እስራኤላውያን አሳደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የግብጽን ንጉሥ የፈርዖንን ልብ አጸና፥ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጸና፤ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ የእስራኤልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንን ልብ አጸና፤ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ የእስራኤልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ። |
ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ”
ስለዚህ ይህን በማድረግ ፈንታ ወደ ቀይ ባሕር በሚያመራው በረሓ፥ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።
ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።
እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።
እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”
በባርነት እንዳትገዙ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ ተጭኖአችሁ የነበረውን የባርነት ቀንበር ሰብሬ፥ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአለሁ።”
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር የወጡት የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን ማለትም በመጀመሪያው የፋሲካ በዓል ማግስት ነበር። ግብጻውያን ሁሉ ፊት ለፊት እያዩአቸው በእግዚአብሔር ጠባቂነት የራምሴን ከተማ ለቀው ወጡ፤
የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ የቀድሞ አባቶቻችንን መረጠ፤ በግብጽ አገር በነበሩበት ጊዜም ትልቅ ሕዝብ አደረጋቸው፤ በታላቅ ኀይሉም ከዚያ አገር አወጣቸው።
እነዚህም ሁሉ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት እንዲገጥሙ እግዚአብሔር ልባቸውን እልኸኛ አድርጎ አነሣሣቸው። ስለዚህም በአጠቃላይ እንዲደመሰሱ ተፈርዶባቸው ያለ ምሕረት ተገደሉ፤ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ ይኸው ነበር።
የያቢን ሠራዊት አዛዥ የሆነው ሲሣራ በቂሾን ወንዝ አንተን ለመውጋት እንዲመጣ አደርጋለሁ፤ እርሱም ሠረገሎቹንና ወታደሮቹን አሰልፎ ይመጣል፤ እኔም በእርሱ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርግሃለሁ።’ ”