Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የእግዚአብሔር ሕግ በከንፈራችሁ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል ለእናንተ በእጃችሁ ላይ እንደ ታሰረ ምልክት፣ በእግራችሁ ላይ እንደሚገኝ መታሰቢያ ይሆንላችኋል። እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ ከግብጽ አውጥቷችኋልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእጅህ እንደ ምልክት በዐይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ፥ የጌታ ሕግ በአፍህ እንዲሆን፥ ጌታ በብርቱ እጅ ከግብጽ አውጥቶሃልና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በበ​ረ​ታች እጅ ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ሃ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ በአ​ፍህ ይሆን ዘንድ በእ​ጅህ እንደ ምል​ክት፥ በዐ​ይ​ኖ​ች​ህም መካ​ከል እንደ መታ​ሰ​ቢያ ይሁ​ን​ልህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር በብርቱ እጅ ከግብፅ አውጥቶሃልና የእግዚአብሔር ሕግ በአፍህ ይሆን ዘንድ በእጅህ እንደ ምልክት በዓይኖችህም መካከል እንደ መታሰቢያ ይሁንልህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 13:9
38 Referencias Cruzadas  

ምልክት ይሆኑህ ዘንድ በእጅህ ላይ እሰራቸው፤ በግንባርህም እንደ መለያ ለጥፋቸው።


ዘርፎቹም እንደማስታወሻ ሆነው ስለሚያገለግሉ፥ እነርሱን በምታዩበት ጊዜ ሁሉ ትእዛዞቼን በማስታወስ ትፈጽማላችሁ፤ ከእኔም ርቃችሁ የገዛ ፈቃዳችሁንና ምኞታችሁን የምትፈጽሙ አትሆኑም፤


ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ”


እኔ እግዚአብሔር ያደረግኹላችሁን ሁሉ በማስታወስ ይህ ቀን መንፈሳዊ ክብረ በዓል ይሁንላችሁ፤ እርሱንም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ እንድታከብሩት ቋሚ ሥርዓት ይሁንላችሁ።”


ደግሞም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “የእግዚአብሔር ቃል አጠገብህ ነው፤ እንዲያውም በአፍህና በልብህ ነው፤” ይህም ቃል እኛ የምናበሥረው የእምነት ቃል ነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከእነርሱ ጋር የሚኖረኝ ቃል ኪዳን ይህ ነው፦ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእናንተ ላይ ያለው መንፈሴና በአንደበታችሁ ያኖርኩትን ቃሌን ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ አስተምሩ ይላል እግዚአብሔር።”


ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ብለው ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የጸሎት ልብሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ፤


ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ትጠብቀውም ዘንድ በአፍህና በልብህ ውስጥ ይገኛል።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”


እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?


ለኢዮአቄም ልጅ ለኢኮንያን እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እኔ ሕያው አምላክ አንተ በቀኝ እጄ እንደሚገኝ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ አውልቄ እጥልሃለሁ፤


እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።


ኢየሩሳሌም ሆይ! እነሆ፥ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽንም ዘወትር አስታውሳለሁ።


እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ለመግዛት ይመጣል፤ የሚመጣውም የሚሰጠውን ሽልማትና የሚከፍለውን የሥራ ዋጋ ይዞ ነው።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።


ልጄ ሆይ! መልካም ጥበብንና አርቆ ማስተዋልን አጥብቀህ ያዝ፤ ከአንተም እንዲርቁ አታድርግ።


እነርሱም ለራስህ ክብርን እንደሚያቀዳጅ ዘውድ፥ ለአንገትህም ውበትን እንደሚሰጥ ሐብል ይሆኑልሃል።


ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤ ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው።


“እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ የአንተ አገልጋዮችና የገዛ ሕዝብህ ናቸው፤ ከዚህ በፊትም በታላቁ ኀይልህና በብርቱ ክንድህ በመታደግ አድነሃቸዋል።


ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች አትርሳ፤


በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው።


ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።


ስለዚህም እጅግ አስፈሪ የሆኑ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ የኀይል ክንዴን ዘርግቼ ግብጻውያንን እቀጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ እንድትወጡ ይፈቅድላችኋል።


እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ።


በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤


በኀያልነቱና በሥልጣኑ ይህን አደረገ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”


አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ።


በግብጽ ምድር ባሪያ የነበርክ መሆንህን አስታውስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይልና በብርቱ ሥልጣን ከዚያ አወጣህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ታከብር ዘንድ ያዘዘህ ስለዚህ ነው።


በዚያን ጊዜ አንተ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ቀድሞ እኛ ለግብጽ ንጉሥ ባርያዎች ነበርን፤ እግዚአብሔር ግን በታላቅ ኀይሉ አወጣን፤


ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ፤ በዚህም ፈንታ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን የውሸት አማልክትን ማገልገል ጀመሩ፤ ለእነርሱም በመስገድ እግዚአብሔርን አስቈጡት።


የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አገር መርቶ አወጣ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


“እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ከዚህ በፊት በብርቱ ኀይልህ ሕዝብህን ከግብጽ በማውጣት ስምህ እስከ ዛሬ ድረስ እንዲታወቅ አድርገሃል፥ እኛ ግን ኃጢአተኞችና በደለኞች ሆንን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios