Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ ይለቅቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በጸ​ናች እጅ ይለ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ልና፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከም​ድሩ አስ​ወ​ጥቶ ይሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና አሁን በፈ​ር​ዖን የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታያ​ለህ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋልና፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።”

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 6:1
27 Referencias Cruzadas  

አገሪቱን ለቀውላቸው እንዲወጡ ግብጻውያን ራሳቸውም ሕዝቡን በማጣደፍ “በአስቸኳይ ለቃችሁ ካልወጣችሁልን እነሆ ሁላችንም ማለቃችን ነው” አሉአቸው።


በኀያልነቱና በሥልጣኑ ይህን አደረገ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።


ከግብጽ በድንገት ተጣድፈው ስለ ወጡ ምግባቸውን ለማዘጋጀትም ሆነ በእርሾ የቦካ እንጀራ ለመጋገር ጊዜ ስላልነበራቸው ከግብጽ ይዘው ካወጡትም ሊጥ ቂጣ ጋገሩ።


በዚያኑ ሌሊት ንጉሡ ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተና እስራኤላውያን ወገኖቻችሁ ሁሉ ከዚህ ውጡ! አገሬን ለቃችሁ ሂዱ! በጠየቃችሁትም መሠረት ለእግዚአብሔር ስገዱ!


“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “በግብጽ ንጉሥና በሕዝቡም ሁሉ ላይ ሌላ መቅሠፍት እልካለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከዚህች ምድር እንድትወጡ ይለቃችኋል፤ እንዲያውም አንድ ሳይቀር ሁላችሁንም ያባርራችኋል።


ለራሱ ዘለዓለማዊ ስም ይሆን ዘንድ በፊታቸው ውሃን ለመክፈል ክብርን የተመላ ኀይሉን በሙሴ ቀኝ በኩል እንዲራመድ ያደረገው የት አለ?


ሥልጣንህ እጅግ የበረታ ነው፤ ኀይልህም እጅግ ታላቅ ነው።


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


በዚህ ጦርነት ላይ የምትዋጉ እናንተ አይደላችሁም፤ ስፍራ ስፍራችሁን ይዛችሁ ብቻ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር ድልን እንደሚያጐናጽፋችሁ ታያላችሁ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! ሳታመነቱና በፍርሃት ሳትሸበሩ ነገ በቀጥታ ሄዳችሁ ተዋጉ! እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ይሆናል!’ ”


ለዚህም ቃል ያ አገልጋዩ የሰጠው መልስ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” የሚል ነበር። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም” ብሎት ነበር።


በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


በያዕቆብ ልጆች ላይ ምንም ዐይነት ጥንቈላ፥ በእስራኤልም ላይ ምንም ዐይነት አስማት አይሠራም፤ እነሆ፥ አሁን ለያዕቆብና ለእስራኤል፥ ‘እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ ተመልከቱ!’ ይባላል።


ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ! ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የሚያደርገውን ዛሬ ታያላችሁ፤ እነዚህን ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ የቀድሞ አባቶቻችንን መረጠ፤ በግብጽ አገር በነበሩበት ጊዜም ትልቅ ሕዝብ አደረጋቸው፤ በታላቅ ኀይሉም ከዚያ አገር አወጣቸው።


እናንተን አይሰማችሁም፤ ከዚያን በኋላ በግብጽ ላይ በታላቅ ፍርድ ብርቱ ቅጣት በማምጣት ሠራዊቴን፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከምድረ ግብጽ አስወጣቸዋለሁ።


በዚህ ዐይነት የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አንሥቼ እስራኤላውያንን ከአገራቸው በማወጣበት ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


“አምላክ ሆይ፥ የቀኝ እጅህ ኀይል፥ ባለ ግርማ ነው፤ ጠላትን ሰባብሮ ይጥላል፤


ይህም በዓል በእጃችሁ እንደ ታሰረ ምልክትና በግንባራችሁ እንዳለ ማስታወሻ ይሆንላችኋል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ስላወጣችሁም የእግዚአብሔር ሕግ ዘወትር ከአንደበታችሁ ሳይለይ በቃላችሁ እንድትደግሙትና እንድታጠኑት ያስታውሳችኋል።


በሚመጡት ዘመናት ልጆችህ የዚህን ሥርዓት ትርጒም ቢጠይቁህ፥ እንዲህ በማለት ታስረዳቸዋለህ፦ ‘በባርነት ከተገዛንበት ከግብጽ ምድር እግዚአብሔር በታላቅ ኀይል አወጣን፤


ይህም ሥርዓት በእጃችን እንደ ታሰረና በግንባራችን ላይ እንደሚገኝ ምልክት ማስታወሻ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ ምድር እንዳወጣንም ያስታውሰናል።’ ”


እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእኔ የእግዚአብሔር ኀይል ውሱን ነውን? ቃሌ በእናንተ ዘንድ የሚፈጸም ወይም የማይፈጸም መሆኑን አሁን ታያለህ!”


የእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች የታመኑ ናቸው፤ በእሳት ምድጃ ሰባት ጊዜ እንደ ነጠረ ብር የጠሩ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios