Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 26:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔርም በታላቅ ኀይሉና ሥልጣኑ ታላቅ ፍርሀትን በማሳደር፥ ሥራዎችን ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን በማሳየት ከግብጽ አወጣን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብጽ አወጣን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከዚያም በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅ ድንጋጤ፥ በተአምራትና በድንቅም ጌታ ከግብጽ አወጣን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ፥ በታ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ትም፥ በድ​ን​ቅም ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 26:8
15 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያንም ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ለመሄድ በእግር ጒዞ ጀመሩ፤ የሰዎቹም ብዛት ሴቶችና ልጆች ሳይቈጠሩ ስድስት መቶ ሺህ ነበር።


አራት መቶ ሠላሳው ዓመት በተፈጸመበትም ቀን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ የግብጽን ምድር ለቆ ወጣ።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር መላውን የእስራኤል ሕዝብ በክፍል በክፍል ከግብጽ ምድር መርቶ አወጣ።


ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህ ቀን በባርነት ስትገዙ የኖራችሁበትን የግብጽን ምድር ለቃችሁ የወጣችሁበት ስለ ሆነ ይህን ቀን አስታውሱ፤ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ በመታደግ ያወጣችሁ በዚህ ቀን ነው፤ ስለዚህ በዚህ ቀን እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ።


ስለዚህም ለእስራኤላውያን የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ግብጻውያን ከሚያደርሱባችሁ የባርነት ጭቈና በማዳን ነጻ አወጣችኋለሁ፤ አሠቃቂ ቅጣት አመጣባቸው ዘንድ የኀይል ክንዴን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ እናንተንም እታደጋችኋለሁ፤


ለራሱ ዘለዓለማዊ ስም ይሆን ዘንድ በፊታቸው ውሃን ለመክፈል ክብርን የተመላ ኀይሉን በሙሴ ቀኝ በኩል እንዲራመድ ያደረገው የት አለ?


በተአምራትና በአስደናቂ ሁኔታ፥ በኀይልህና በታላቅነትህ፥ እንዲሁም በአስፈሪ ግርማህ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አወጣህ፥


እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ግብጽ ንጉሥና ወደ መኳንንቱ እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ ልኮ በእርሱ አማካይነት እንዲፈጸሙ ያደረጋቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ያሳየ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም።


ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት ያደረገውን ዐይነት ታላቅና አስፈሪ ነገር ሁሉ ያደረገ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


በግብጽ ምድር ባሪያ የነበርክ መሆንህን አስታውስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይልና በብርቱ ሥልጣን ከዚያ አወጣህ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ታከብር ዘንድ ያዘዘህ ስለዚህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos