ኤፌሶን 4:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ ወዲያ አይስረቅ፤ ይልቅስ ለችግረኞች ይሰጥ ዘንድ ገንዘብ እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካም ነገርን ይሥራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሰርቅ የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ለተቸገሩት የሚያካፍለው ነገር እንዲኖረው በገዛ እጆቹ በጎ የሆነውን እየሠራ ለማግኘት ይድከም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚሰርቅም እንግዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን ድሃውን ይረዳ ዘንድ በእጆቹ መልካም እየሠራ ይድከም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። |
ብዙ ሀብት ቢኖረኝ “እግዚአብሔር ማን ነው?” ብዬ አንተን እስከ መካድ እደርሳለሁ፤ ድኻ ብሆን ደግሞ እሰርቅ ይሆናል፤ በዚህም ሁኔታ የአንተን የአምላኬን ስም አሰድባለሁ።
ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የተጠቀለለው መጽሐፍ በውስጡ በምድሪቱ ሁሉ ላይ የሚመጣው ርግማን ተጽፎበታል፤ የተጠቀለለው መጽሐፍ በአንድ በኩል ‘ሌባ ሁሉ ከምድር ይወገዳል’ የሚል ሲሆን፥ በሌላ በኩል ‘በመሐላ ሐሰት የሚናገር ሁሉ ይጠፋል’ ይላል።
ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታ ኢየሱስን እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ ካለኝ ሀብት ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ በማታለል ከሰው ላይ የወሰድኩትም ገንዘብ ቢኖር፥ አራት እጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ።”
ይልቁንስ ንስሓ መግባታችሁን የሚያመለክት ሥራ ሥሩ እንጂ እኛ የአብርሃም ልጆች ነን እያላችሁ በልባችሁ አትመኩ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እንደሚችል እነግራችኋለሁ።
እርሱ ይህን የተናገረው፥ ለድኾች አዝኖ ሳይሆን፥ ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢት የሚይዝ እርሱ በመሆኑ በከረጢቱ የሚከተተውን ገንዘብ መውሰድ ለምዶ ነበር።
ይሁዳ ገንዘብ ያዥ ስለ ነበረ ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ ኢየሱስ “ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ ወይም ለድኾች ምጽዋት ስጥ” ያለው መስሎአቸው ነበር።
ይህ የታመነ አባባል ነው። በእግዚአብሔር ያመኑ ሰዎች ለመልካም ሥራ እንዲተጉ ይህን ነገር ሁሉ በጥብቅ እንድታስገነዝብ እፈልጋለሁ፤ ይህም ነገር መልካምና ለእያንዳንዱ ሰው ጠቃሚ ነው።