እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
ዘዳግም 4:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሌሎች ሕዝቦች መካከል ይበታትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እናንተን በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚበትናችሁ አሕዛብ መካከል የምትተርፉት ጥቂቶቻችሁ ብቻ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ ጌታ በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም በቍጥር ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። |
እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
ያዕቆብ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቊጥር አነስተኞች ነን፤ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”
እነርሱም “ተማርከው ወደ ባቢሎን ሳይወሰዱ የቀሩትና በሕይወት ያሉት አይሁድ በታላቅ ችግርና ኀፍረት ላይ ወድቀው ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጽሮች ፈራርሰው ወድቀዋል፤ የቅጽር በሮቹም በእሳት ጋይተዋል” ሲሉ መለሱልኝ።
እስራኤል በላይኛው ቅርንጫፍ ላይ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬዎች ብቻ እንዳሉት፥ እንዲሁም በታችኛው ቅርንጫፉ ላይ አራት ወይም አምስት ፍሬዎች እንደ ቀሩበት የወይራ ዛፍ ትሆናለች፤ ሆኖም ጥቂት ሕዝቦች ይተርፋሉ። እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ስለዚህ ከዚህች አገር አውጥቼ፥ እናንተም ሆናችሁ የቀድሞ አባቶቻችሁ ወደማያውቁት አገር እወረውራችኋለሁ፤ እዚያም ሐሰተኞች አማልክትን ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ፤ ፈጽሞ ምሕረት አላደርግላችሁም።’ ”
ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሩቅ አገር በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል እንዲኖሩ ባደርጋቸውና በተለያዩ አገሮች ብበትናቸውም እንኳ ለጥቂት ጊዜ ግን መገናኛቸው ቤተ መቅደስ እሆንላቸዋለሁ።
“የሜሼክና የቱባል ወታደሮች ሕዝቦቻቸው መቃብሮች በዚያ ነበሩ፤ እነርሱ የተገደሉት በጦርነት ነው፤ ሁሉም በእግዚአብሔር ያላመኑ ናቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱም ከዚህ በፊት የሕያዋንን ዓለም የሚያሸብሩ ነበሩ።
ጌታ ሆይ! አንተ እውነተኛ ነህ፤ ነገር ግን ለአንተ ታማኞች ባለመሆናችን፥ እኛ በምድር ሁሉ ላይ የበተንከን በቅርብና በሩቅ ያለን የይሁዳ ሕዝብ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና መላዋ የእስራኤል ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ኀፍረት ደርሶብናል።
በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤
እንደ ዐውሎ ነፋስ ጠራርጌ በመውሰድም በማያውቁት ባዕድ አገር እንዲኖሩ አደረግኋቸው፤ ይህችም መልካም ምድር ማንም የማይኖርባት ባድማ ሆና ቀረች፥ ያቺ ያማረች ምድርም ባድማ ሆነች።”
“እግዚአብሔር አንተንና ንጉሥህን ከዚህ በፊት የቀድሞ አባቶችህም ሆኑ አንተ ወዳልነበራችሁበት ባዕድ አገር አፍልሶ ይወስዳችኋል፤ በዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ባዕዳን አማልክትን ታመልካላችሁ።
እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’