Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 44:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ሕዝብህን በአነስተኛ ዋጋ ሸጥከው፤ እርሱንም በመሸጥ ምንም አላተረፍክም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥ ወደ አሕዛብም በተንኸን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 44:12
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “በመላ ሀገሪቱ በፈጸማችሁት ኃጢአት ምክንያት ሀብታችሁንና ንብረታችሁን ያለ አንዳች ማካካሻ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ።


ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል? ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ?


ቀረፋ፥ ቅመም፥ የሚሸት እንጨት፥ ከርቤ፥ ዕጣን፥ ወይን ጠጅ፥ የወይራ ዘይት፥ ዱቄት፥ ስንዴ፥ ከብቶች፥ በጎች፥ ፈረሶች፥ ሠረገላዎች፥ ባርያዎችና ሌሎችም ሰዎች ናቸው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንድ ሚስቱን ፈቶ እንደሚያባርር እኔ እናንተን ሕዝቤን ያባረርኩ ይመስላችኋልን? ይህስ ከሆነ የፍችው ደብዳቤ የት አለ? ሰው ልጆቹን ለባርነት እንደሚሸጥ እኔም እናንተን ለምርኮ አሳልፌ የሸጥኳችሁ ይመስላችኋልን? ከሆነስ ለማንኛውም አበዳሪዬ ሸጥኳችሁ? እናንተ ለምርኮ የተሰጣችሁት በኃጢአታችሁ ምክንያት ነው፤ የተሰደዳችሁትም በፈጸማችሁት በደል ነው።


ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤


ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በጣም ተቈጣ፤ እንዲዘርፉአቸውም ለወራሪዎች አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ያሉ ጠላቶቻቸውም እንዲበረቱባቸው አደረገ። ከዚያም በኋላ እስራኤላውያን ከጠላቶቻቸው ወረራ ራሳቸውን መከላከል ተሳናቸው።


በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤


እግዚአብሔር በሌሎች ሕዝቦች መካከል ይበታትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios