እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።
ዘዳግም 34:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞአብ ምድር ሳለ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት በዚያ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ባርያም ሙሴ እንደ ጌታ ቃል በሞዓብ ምድር ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ባሪያም ሙሴ እንደ እግዚአብሔር ቃል በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ። |
እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረውም ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፤ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ እግር ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ፤ ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር።
በገባዖን ወደሚገኘው ኰረብታማ የማምለኪያ ስፍራ አብረውት እንዲሄዱ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወደዚያ የሄዱበትም ምክንያት፥ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው፥ እግዚአብሔር የሚመለክበት ድንኳን በዚያው በገባዖን ስለሚገኝ ነው።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ የመሞቻህ ጊዜ ደርሶአል፤ የሚመራበትን ትእዛዝ እሰጠው ዘንድ ኢያሱን ጠርተህ አንተና እርሱ ወደ መገናኛው ድንኳን ቅረቡ፤” ሙሴና ኢያሱም አብረው ወደ መገናኛው ድንኳን ቀረቡ፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።
እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል።
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው ጽድቅ አማካይነት እኛ እንዳገኘነው እምነት ያለ የከበረ እምነት ላገኛችሁት፤
የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤