Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 31:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ በቅርብ ጊዜ እንደ ቀድሞ አባቶችህ ትሞታለህ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ሕዝብ ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳል። እኔንም በመተው በሚወርሰው ምድር የሚገኙትን ጣዖቶች ያመልካል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፤ ከአባቶችህ ጋራ ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋራ የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ ባዕዳን አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል። እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ታን​ቀ​ላ​ፋ​ለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነ​ሣል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ትም ዘንድ በሚ​ሄ​ድ​ባት ምድር መካ​ከል ያሉ​ትን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ትሎ ያመ​ነ​ዝ​ራል፤ እኔ​ንም ይተ​ወ​ኛል፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን ያፈ​ር​ሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፥ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፥ እኔንም ይተወኛል፥ ከእነርሱም ጋር ያደርግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 31:16
44 Referencias Cruzadas  

እስራኤላውያን ባዓልና ዐስታሮት የተባሉትን ባዕዳን አማልክት እንዲሁም የሶርያን፥ የሲዶናን፥ የሞአብን፥ የዐሞንንና የፍልስጥኤምን አማልክት በማምለክ እንደገና እግዚአብሔርን በደሉ፤ እርሱንም ማምለክ ተዉ፤


እናንተ ግን እስከ አሁን ድረስ እኔን ትታችሁ ለባዕዳን አማልክት ሰገዳችሁ፤ ስለዚህ እኔ እናንተን ዳግመኛ አልታደጋችሁም፤


ከግብጽ ያወጣቸውን የቀድሞ አባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ማገልገል ተዉ፤ በዚህም ፈንታ በዙሪያቸው ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኩአቸውን የውሸት አማልክትን ማገልገል ጀመሩ፤ ለእነርሱም በመስገድ እግዚአብሔርን አስቈጡት።


ለከንቱ አማልክታቸው ሲሰግዱና መሥዋዕት ሲሠዉላቸው እንድትተባበሩአቸው ስለሚጠይቁአችሁ፥ እናንተም እነርሱ ለአማልክታቸው የሚያቀርቡትን ምግብ ለመብላት ስለምትፈተኑ፤ በአገሩ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ።


ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው፤ ምድርን በአመንዝራነትዋ ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ በፍርድ ቀጥቶአታል፤ እርስዋን በመቅጣትም የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።”


“ነገር ግን በውበትሽና በዝናሽ ተማምነሽ ከዐላፊ አግዳሚ ሁሉ ጋር የዝሙት ሥራ ፈጸምሽ።


“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም። በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤ የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤ መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።


ነገር ግን ዳዊት በሕይወቱ ዘመን አገልግሎቱን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከፈጸመ በኋላ ሞቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮአል፤ መበስበስም ደርሶበታል።


ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።


ይህም ቃል ኪዳን እነርሱን ከግብጽ ለማውጣት እጃቸውን በያዝኩ ጊዜ እንደ ገባሁት ቃል ኪዳን ያለ አይደለም፤ እኔ አምላካቸው ብሆንም እንኳ እነርሱ ቃል ኪዳኔን አልጠበቁም፤ እኔም ችላ አልኳቸው፤


እነርሱ በሥራቸው ረከሱ፤ በክፉ ሥራቸውም እግዚአብሔርን ካዱ።


እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤ አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።


ኀይል የተሞላው የወጣትነት ሰውነቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዐፈር ይሆናል።


ትእዛዞቼን ባትጠብቁ፥ ሕግጋቴን ብትንቁ፥ ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱና ሥርዓቶቼን ብትጸየፉ፥


በማግስቱ ሰዎቹ ተነሥተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ እነርሱም ተቀምጠው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ።


በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤


አንተ ግን ብዙ ዘመን ኖረህ በሰላም ትሞታለህ፤ በሰላምም ትቀበራለህ።


አባቶቼ በተቀበሩበት መቃብር መቀበር ስለምፈልግ በምሞትበት ጊዜ ከግብጽ አገር ወስደህ፥ እነርሱ በተቀበሩበት ስፍራ ቅበረኝ።” ዮሴፍም “እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው።


“ልጆችና የልጅ ልጆች ኖሮአችሁ በምድሪቱ በደስታ በምትኖሩበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን በምንም ዐይነት ቅርጽ ጣዖት በመሥራት ረክሳችሁ እግዚአብሔርን አታስቈጡት፤


ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ክፉ ሥራ በመሥራት እግዚአብሔርን በደሉ። በዓሊም ተብለው የሚጠሩትን ባዕዳን አማልክት አመለኩ፤


ይህን ባታደርግ ግን አንተ ከሞትህ በኋላ ወዲያውኑ ልጄ ሰሎሞንና እኔ እንደ በደለኞች እንቈጠራለን።”


ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም!


ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።


እግዚአብሔር አስፈሪ በሆነው ቊጣና መዓቱ ሕዝቡን እንደሚቀጣ የተናገረ በመሆኑ ምናልባት በመጸጸት ከክፉ ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይለምኑት ይሆናል።”


እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን ማስተላለፍ ሲጀምር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቤ ከእኔ ተለይቶ አጸያፊ የሆነ የዝሙት ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛል፤ እንግዲህ አንተም ሂድና ዘማዊት ሴት አግባ፤ ከእርስዋም የዝሙት ልጆችን ውለድ።”


በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል።


ያዕቆብ የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ ምድር እንዳትቀብረኝ፥ እጅህን በጒልበቴ ላይ አኑረህ በመሐላ ቃል ግባልኝ።


እርሱንም ካየህ በኋላ ወንድምህ አሮን እንደ ሞተ አንተም ትሞታለህ፤


ባዕዳን አማልክትን በማምለክ በሠሩት ኃጢአት እኔ በዚያ ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።


ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤


ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞአብ ምድር ሳለ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት በዚያ ሞተ።


ሰማርያ የወደቀችበት ምክንያት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ነው፤ ይኸውም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አፈረሱ፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ በሆነው በሙሴ አማካይነት ለተሰጠ ሕግ ሁሉ ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ቃሉን ማዳመጥም ሆነ ሕጉን መጠበቅ አልፈለጉም።


በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለመሞት ተቃርቦ ነበር፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጐበኘው ሄዶ “እግዚአብሔር ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ሁሉን ነገር አስተካክል’ ብሎሃል” ሲል ነገረው።


እርሱ በይሁዳ ኰረብቶች ላይ ሳይቀር እንኳ የአሕዛብ የማምለኪያ ስፍራዎችን ሠራ፤ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ወደ ኃጢአት በመምራት እግዚአብሔርን እንዲያሳዝኑ አደረገ።


እኔ የምናገረውን አትሰሙም፤ ለማወቅም አትፈልጉም፤ ከጥንት ጀምሮ ጆሮአችሁ የተደፈነ ነው፤ ይህም የሆነው እናንተ በጣም ከዳተኞች መሆናችሁንና ከተወለዳችሁ ጀምሮ ዐመፀኞች ተብላችሁ መጠራታችሁን ዐውቃለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios