ዘዳግም 25:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክህ ምድሪቱን አውርሶህ በዙሪያህ ከሚኖሩ ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ በምድር ላይ ማንም የሚያስታውሳቸው እስኪጠፋ ድረስ ዐማሌቃውያንን ሁሉ ደምስስ! ይህን ከቶ አትርሳ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፣ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስስ፤ ከቶ እንዳትረሳ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ ባሳረፈህ ጊዜ፥ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ መደምሰስን፥ ይህንን አትርሳ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የዐማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንም አትርሳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የአማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንን አትርሳ። |
ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ የሃመዳታ ልጅ የሆነውን አጋጋዊውን ሐማንን ከሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በላይ ክብሩን በማስበለጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾመው።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።
በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር የተረገመ ስለ ሆነ አስከሬኑ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ አይደር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በርስትነት የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ አስከሬኑን በዚያኑ ዕለት ቅበረው።
“በዚህም ጊዜ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ይህን ምድር ትወርሱ ዘንድ ሰጥቶአችኋል፤ እንግዲህ የጦር ሰዎቻችሁን አስታጥቃችሁ ሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ምድራቸውን እስኪወርሱ ድረስ እነርሱን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው እንዲዘምቱ አድርጉ።
እንግዲህ ተወኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም ሊያስታውሳቸው በማይችል ሁኔታ ልደምስሳቸው፤ ከዚያም በኋላ አንተን ከእነርሱ ይበልጥ ኀይልና ብዛት ላለው ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።’
እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ምድሩን ሁሉ በእጁ አደረገ፤ ለእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ድርሻ ርስት አድርጎ በመስጠት ለእስራኤላውያን በሙሉ አከፋፈለ። ስለዚህም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
ከብዙ ጊዜ በኋላ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በዙሪያቸው ከሚገኙ ጠላቶቻቸው በማሳረፍ የሰላምን ኑሮ ሰጣቸው። በዚያን ጊዜ ኢያሱ በዕድሜው ሸምግሎ ነበር፤
እስራኤላውያን ጠላቶቻቸውን መቋቋም ያልቻሉበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እነርሱ ራሳቸው እንዲጠፉ ስለ ተፈረደባቸው ከጠላቶች ፊት ወደ ኋላ ይሸሻሉ። እንዲደመሰስ የታዘዘውን ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ እኔ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
በዚያን ጊዜ ውስጥ ዳዊትና ተከታዮቹ በጌሪሹራውያን፥ በጌዛውያንና በአማሌቃውያን ላይ ዘመቱ፤ እነዚህም አገሮች ከቴሌኦም ጀምሮ ወደ ሱርና ወደ ምድረ ግብጽ የሚወስዱ እነርሱ የሚኖሩባቸው አገሮች ነበሩ።