በማለዳ እየተነሣ በመሄድ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር በሚያስገባው መንገድ ዳር ይቆም ነበር፤ ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያይለት የሚፈልግ ጠብ ክርክር ያለበት ሰው ሁሉ ወደዚያ ሲመጣ አቤሴሎም ጠርቶ ከወዴት እንደ መጣ ይጠይቀዋል፤ ሰውየው ከየትኛው ነገድ መሆኑን ከነገረው በኋላ፥
ዘዳግም 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በደም ማፍሰስ፥ በሰብአዊ መብት፥ በግድያ ወይም እነዚህን በመሳሰሉ ጉዳዮች በከተሞችህ በሚነሡ ክርክሮች የፍርድ አሰጣጡ አስቸጋሪ ቢሆንብህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ቦታ ፈጥነህ በመሄድ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንድ የነፍስ ግድያ ዐይነትና በሌላ፣ በአንድ ዐይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፣ ወይም በአንድ የክስ ዐይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጕዳይ ቢነሣ፣ ከዐቅምህ በላይ የሆነ ጕዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፣ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ውጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ፥ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፥ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅምህ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፥ ተነሥተህ አምላክህ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ውጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በደምና በደም መካከል፥ በፍርድና በፍርድ መካከል፥ በመቍሰልና በመቍሰል መካከል፥ በክርክርና በክርክር መካከል በሀገርህ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢኖር፥ አንተ ተነሥተህ ስሙ በዚያ ይጠራ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደምና በደም፥ በፍርድና በፍርድ፥ በመቁሰልና በመቁሰል መካከል በአገርህ ደጅ ውስጥ ሰዎች ስለሚከራከሩበት ክርክር የሚሳንህ የፍርድ ነገር ቢነሣ፥ አንተ ተነሥተህ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ትወጣለህ፤ |
በማለዳ እየተነሣ በመሄድ ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር በሚያስገባው መንገድ ዳር ይቆም ነበር፤ ንጉሡ ጉዳዩን እንዲያይለት የሚፈልግ ጠብ ክርክር ያለበት ሰው ሁሉ ወደዚያ ሲመጣ አቤሴሎም ጠርቶ ከወዴት እንደ መጣ ይጠይቀዋል፤ ሰውየው ከየትኛው ነገድ መሆኑን ከነገረው በኋላ፥
ሙሴም ለዐማቱ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት ሕዝቡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ወደ እኔ ስለሚመጣ ነው፤
እነርሱም ከባድ ያልሆኑ ጉዳዮችን በማየት ሕዝቡን ሁልጊዜ በዳኝነት ያገለግሉ ጀመር፤ አስቸጋሪ የሆኑትን ጉዳዮች ብቻ ወደ ሙሴ ሲያቀርቡ፥ ቀላል የሆነውን ጠብና ክርክር ሁሉ ራሳቸው ይወስኑ ነበር።
“ሁለት ሰዎች ሲጣሉ አንዲት ነፍሰ ጡር መተው ቢያስወርዳትና ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስባት ቢቀር፥ ያ ጒዳት ያደረሰባት ሰው የሴቲቱ ባል የሚጠይቀውን ያኽል ካሣ ይክፈል፤ ይህም የሚከፍለው ካሣ መጠን በዳኞች የጸደቀ ይሁን።
ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለው ቢያጣ በባሪያነት ይሸጥ፤ የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት በእጁ ቢገኝ ለያንዳንዱ እንስሳ እጥፍ ዋጋ ይክፈል። “አንድ ሌባ ቤት ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመትቶ ቢገደል ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ አይሆንም። ሌባው ሰብሮ የገባው ፀሐይ ከወጣ በኋላ ሆኖ ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ ይሆናል።
ሌባው ካልተገኘ ግን ዕቃውን በዐደራ የተቀበለው ሰው የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ዳኞች ፊት ቀርቦ የዚያን ሰው ንብረት አለመስረቁን በመሐላ ያረጋግጥ።
ሕግን በሚመለከት አከራካሪ ነገር በሚነሣበት ጊዜ፥ ደንቡ በሚያዝዘው መሠረት ካህናቱ ይወስኑላቸው፤ በሕጌና ሥርዓቴ መሠረት በዓሎቼን፥ እንዲሁም ዕለተ ሰንበትን በመቀደስ ይጠብቁ።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
ከዚያም እኔ ያዘዝኳችሁን ነገር ሁሉ የምታመጡት እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ መጠሪያ ወደ መረጠው ቦታ ይሆናል፤ ይኸውም የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና ሌላውንም መሥዋዕታችሁን ሁሉ፥ ዐሥራታችሁንና መባችሁን ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር የተሳላችሁትን የበጎ ፈቃድ ስጦታችሁን ሁሉ ታመጡለታላችሁ።
መሥዋዕትህን ሁሉ ማቅረብ የሚገባህ ከነገዶችህ መካከል የአንዱ ግዛት በሆነው ክፍል እና እግዚአብሔር በሚመርጠው በአንድ ስፍራ ብቻ ነው፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህንም ሆነ ሌላውንም እኔ ያዘዝኩህን ሁሉ በዚያ ስፍራ ብቻ ትፈጽማለህ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤
አንድ ሰው ቀድሞ ጠላት ያልነበረውን አንድ ሰው የገደለው ሆን ብሎ በማሰብ ሳይሆን በአጋጣሚ አደጋ ምክንያት ሆኖ ከተገኘ አምልጦ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ በመግባት ሕይወቱን ያትርፍ።
እርሱን እንዲያገለግሉት፥ በእርሱ ስም እንዲባርኩ፥ የክርክርና የወንጀል ጉዳይ በእነርሱ እንዲወሰን አምላክህ እግዚአብሔር ካህናቱን የሌዊን ልጆች ስለ መረጣቸው ወደ አስከሬኑ ይቅረቡ።