ንጉሥ አካዝ ወደ ደማስቆ ሄዶ ከንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ጋር በተገናኘ ጊዜ በዚያ አንድ መሠዊያ አየ፤ ያንን መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኡሪያ ላከለት፤
ዘዳግም 12:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሕዝቦች ከተደመሰሱ በኋላ እነርሱ ያደርጉ የነበረውን ድርጊት በማድረግ ወጥመድ ውስጥ አትግባ፤ እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ በማለት እነዚህ አሕዛብ አማልክቶቻቸውን እንዴት ያመልኩ ነበር ብለህ አትጠይቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፣ “እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ” ብለህ በመጠየቅ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊትህ ከጠፉ በኋላ፥ ‘እነዚህ ሕዝቦች አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ’ ብለህ በመጠየቅ እንዳትጠመድ ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላኮቻቸውንም እንዳትሻ፥ አሕዛብም ለአምላኮቻቸው እንደሚያደርጉ እኔም አደርጋለሁ እንዳትል ራስህን ጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድራቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥ ከፊትህ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመድ፦ እነዚህስ አሕዛብ አማልክቶቻቸውን ያመለኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔ አደርጋለሁ ብለህ ስለ አማልክቶቻቸው እንዳትጠይቅ ተጠንቀቅ። |
ንጉሥ አካዝ ወደ ደማስቆ ሄዶ ከንጉሠ ነገሥት ቲግላት ፐሌሴር ጋር በተገናኘ ጊዜ በዚያ አንድ መሠዊያ አየ፤ ያንን መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኡሪያ ላከለት፤
የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።
ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን አካሄድ አትከተሉ፤ መቼም አሕዛብ ያልተለመደ አዲስ ነገር በሰማይ ባዩ ጊዜ በፍርሃት መንቀጥቀጥ ልማዳቸው ነው፤ እናንተ ግን በዚህ አትሸበሩ።
ለእነርሱ እንደምሰጣቸው ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር አመጣኋቸው፤ ይሁን እንጂ እነርሱ ከፍተኛ ኰረብቶችንና ለምለም ዛፎችን ባዩ ጊዜ በሁሉም ላይ መሥዋዕት አቀረቡ፤ በሚቃጠል መሥዋዕታቸው፥ መዓዛው በሚጣፍጥ ዕጣናቸውና ለመሥዋዕትም በሚያፈሱት የመጠጥ ቊርባናቸው አስቈጡኝ፤
እንደ ሌሎች ሕዝቦች ወይም ለዛፍና ለድንጋይ እንደሚሰግዱ በሌሎች አገሮች እንደሚኖሩ አሕዛብ ለመሆን ወስናችኋል፤ ነገር ግን ይህ ከቶ ሊሆን አይችልም።’ ”
በኖራችሁባት በግብጽ ምድር፥ ወይም አሁን እኔ በማስገባችሁ በከነዓን ምድር የሚኖሩ አሕዛብ የሚያደርጉትን አታድርጉ፤ ሥርዓታቸውንም አትከተሉ።
“እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዝ ሁሉ ፈጽሙ፤ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ይፈጽሙት የነበረውን የረከሰ ልማድ አትከተሉ፤ ከእነዚህ አሳፋሪ ተግባሮች አንዱንም በመፈጸም ራሳችሁን አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”
በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ አስወጡአቸው፤ ከድንጋይና ከብረት የተሠሩትን ጣዖቶቻቸውንም ሰባበሩ፤ በኮረብታ ላይ ያሉ መስገጃዎቻቸውንም አፈራርሱ።
መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።
አንተ ለእግዚአብሔር ለአምላክህ የምትሰግድለት፥ እነዚህ አሕዛብ ለባዕዳን አማልክታቸው በሚሰግዱላቸው ዐይነት መሆን የለበትም፤ እነርሱ ለባዕዳን አማልክቶቻቸው በሚሰግዱበት ጊዜ የሚፈጽሙት ነገር ሁሉ እጅግ አጸያፊና በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው፤ እነርሱ ሌላው ቀርቶ የገዛ ልጆቻቸውን በመሠዊያዎቻቸው ላይ ለአማልክታቸው በእሳት ያቃጥላሉ።
ይህንንም የምታደርጉት ለባዕዳን አማልክቶቻቸው ስለ መስገድ አጸያፊ የሆነውን ነገር ሁሉ ለእናንተ በማስተማር እግዚአብሔር የሚጠላውን ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጉአችሁ ነው።