“ሕዝብህ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ፥ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፥
ዘዳግም 11:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ባዕዳን አማልክትን ለመከተልና ለማምለክ ዘወር እንዳትሉ ተጠንቀቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ተታልላችሁ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ፤ ትሰግዳላችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተጠንቀቁ! ተታላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ፤ እንዳትሰግዱላቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥ |
“ሕዝብህ በደል ሠርተው አንተን በማሳዘናቸው ምክንያት ዝናብ እንዳይዘንብላቸው አድርገህ በምትቀጣቸው ጊዜ፥ በፈጸሙት በደል በመጸጸት ፊታቸውን ወደዚህ ቤተ መቅደስ መልሰው በትሕትና ቢለምኑህ፥
ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።
እነዚህ ሕዝቦች ከተደመሰሱ በኋላ እነርሱ ያደርጉ የነበረውን ድርጊት በማድረግ ወጥመድ ውስጥ አትግባ፤ እኔም እንደ እነርሱ አደርጋለሁ በማለት እነዚህ አሕዛብ አማልክቶቻቸውን እንዴት ያመልኩ ነበር ብለህ አትጠይቅ።
በዚህ ከቆማችሁት መካከል ማንም ወንድ ወይም ሴት፥ ቤተሰብ ወይም ነገድ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ በማለት የሌሎችን ሕዝቦች አማልክት የሚከተል እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ በመካከላችሁ እንደዚህ ያለ መርዘኛና መራራ የሆነ ሥራ የሚሠራ አይኑር፤
ለቀድሞ አባቶቻቸው በመሐላ ቃል ኪዳን በገባሁላቸው መሠረት በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ምድር አስገባቸዋለሁ፤ በዚያም በልተው በጠገቡና በወፈሩ ጊዜ እኔን ይተዋሉ፤ ቃል ኪዳኔንም አፍርሰው ሌሎች አማልክትን ያመልካሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እርግጠኞች ሁኑ፤ ምንም ዐይነት የተቀረጸ ምስል እንዳትሠሩ፤ የነገራችሁንም ትእዛዝ ፈጽሙ።
እንግዲህ በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን በዐይናችሁ ያያችሁትን ሁሉ እንዳትረሱና ከአእምሮአችሁ እንዳይጠፋ ተጠንቀቁ። ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤
እግዚአብሔር አምላክህን ብትረሳና ትሰግድላቸውና ታገለግላቸውም ዘንድ ወደ ባዕዳን አማልክት ፊትህን ብትመልስ፥ በእርግጥ የምትጠፋ መሆንህን ዛሬውኑ አስጠነቅቅሃለሁ።
ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጐድልበት ተጠንቀቁ፤ እንዲሁም ምንም መራራ ፍሬ የሚያፈራ ሥር በመካከላችሁ እንዳይበቅልና እንዳያስቸግራችሁ ብዙዎችንም እንዳያረክስ ተጠንቀቁ።
ስለዚህ እርሱ ወደሚሰጠን የዕረፍት ቦታ ለመግባት የተቀበልነው ተስፋ ገና የጸና ስለ ሆነ ከእናንተ ማንም ወደዚህ የዕረፍት ቦታ የመግባት ዕድል ሳያገኝ እንዳይቀር ሁላችንም እንጠንቀቅ።
ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።
ከዚህ በኋላ ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው አየሁ፤ ስለ ኢየሱስ በመመስከራቸውና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሶች አየሁ፤ እነርሱ ለአውሬውና ለምስሉ ያልሰገዱ፥ ምልክቱንም በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያላደረጉ ናቸው፤ እነርሱ ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ነገሡ።
ሳሙኤልም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ ይህን የመሰለ ክፉ ነገር ያደረጋችኹ ብትሆኑ እንኳ በሙሉ ልባችሁ እርሱን አገልግሉት እንጂ ፊታችሁን ከእግዚአብሔር ወደ ሌላ አትመልሱ።