አሞጽ 8:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለያዕቆብና ለዘሮቹ መመኪያ የሆነው እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ማለ፦ “እነርሱ የሠሩትን ሥራ ሁሉ አልረሳም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነርሱ ያደረጉትን ሁሉ ከቶ አልረሳም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በያዕቆብ ሞገስ እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ “ሥራቸውን ሁሉ ለዘለዓለም በፍጹም አልረሳም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በያዕቆብ ትዕቢት እንዲህ ብሎ ምሎአል፥ “ሥራችሁን ሁሉ ለዘለዓለም ምንም አልረሳም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በያዕቆብ ክብር እንዲህ ብሎ ምሎአል፦ ሥራቸውን ሁሉ ለዘላለም ምንም አልረሳም። |
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ ነግሮኛል፦ “በሕይወት እስካሉ ድረስ ይህ ክፉ በደል አይሰረይላቸውም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ኃጢአታችሁ በብረት ብዕር ተጽፎአል፤ ሹል በሆነው አልማዝ በልባችሁ ጽላትና በመሠዊያዎቻችሁ ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል።
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
“እናንተና የቀድሞ አባቶቻችሁ፥ ንጉሦቻችሁና መሪዎቻችሁ፥ በምድሪቱም የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ዕጣን ታጥኑ እንደ ነበረ፥ እግዚአብሔር አያስበውም ወይም ረስቶታል ብላችሁ ታስባላችሁን?
ነገር ግን እኔ ይህን ሁሉ ክፋታቸውን እንደማስታውስ ከቶ አይገነዘቡም፤ ከዚህ የተነሣ በገዛ ኃጢአታቸው ተከበዋል፤ ክፉ ሥራቸው ሁሉ ከእኔ የተሰወረ አይደለም።”
እነርሱ ለእኔ ምርጥ መሥዋዕት ቢያቀርቡ፥ የመሥዋዕቱንም ሥጋ ቢበሉ እኔ እግዚአብሔር አልቀበላቸውም። አሁን በደላቸውን አስቤ በኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፦ “እናንተ በመንጠቆ ተይዞ እንደሚወሰድ ነገር የምትወሰዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ከእናንተ እስከ መጨረሻ የቈዩት እንኳ በመንጠቆ ተይዘው እንደሚወሰዱ ዐሣዎች ይወሰዳሉ።
የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር “የእስራኤልን ሕዝብ ትዕቢት ጠልቼአለሁ፤ የተዋቡ ቤተ መንግሥቶቻቸውን ተጸይፌአለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ከተማይቱንና በእርስዋ የሚኖሩትን ሁሉ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሎአል።