2 ሳሙኤል 24:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ሕዝቡን ይቀሥፍ የነበረውን መልአክ አይቶ እግዚአብሔርን “በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ እኔም ራሴ ክፉ ነገርን አደረግሁ፤ ታዲያ ይህ ምስኪን ሕዝብ ምን በደለህ? ይህ መቅሠፍት በእርሱ ላይ ከሚወርድ ይልቅ በእኔና በቤተሰቤ ላይ ይሁን” ሲል ጠየቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፣ “እነሆ ኀጢአት የሠራሁትም የተሳሳትሁም እኔ ነኝ፤ እነዚህ ግን በጎች ናቸው፤ ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ ባየ ጊዜ ጌታን፥ “እነሆ፥ ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ! የተሳሳትሁም እኔ ነኝ! እነዚህ በጎች ግን ምን አጠፉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድያለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ተናገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፦ እነሆ፥ እኔ በድያለሁ ጠማማም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፥ እነዚህ በጎች ግን እነርሱ ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ እንድትሆን እለምንሃለሁ ብሎ ተናገረው። |
ነገር ግን ዳዊት ሕዝቡን ከቈጠረ በኋላ የኅሊና ወቀሳ ስላስጨነቀው እግዚአብሔርን “እኔ ይህን በማድረጌ ታላቅ በደል ፈጽሜአለሁ፤ የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራሁም እባክህ ይቅር በለኝ!” ሲል ለመነ።
“ስለዚህም ለአገልጋዬ ለዳዊት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ አንተን የበግ መንጋ ከምትጠብቅበት መስክ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤
ሚክያስም “መላው የእስራኤል ሠራዊት ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች በኮረብታዎች ላይ ተበታትነው አያለሁ፤ እግዚአብሔርም ‘እነዚህ ሰዎች መሪ የላቸውም፤ ስለዚህ ወደየቤታቸው በሰላም ይመለሱ ብሎአል’ ሲል መለሰለት።”
አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
ዮናስም “ይህ ማዕበል በእናንተ ላይ የመጣው በእኔ በደል ምክንያት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ እኔን አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፤ ማዕበሉም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ሙሴና አሮን በግንባራቸው ወደ መሬት ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ የሕይወት ሁሉ ምንጭ ነህ፤ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?”