Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ንጉሡም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “አምላካችሁን እግዚአብሔርንና እናንተን በድያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያም ፈርዖን ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔር በእናንተም ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠራና እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ አምላካችሁንና እናንተን በደልሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን በፍ​ጥ​ነት ጠራ፥ “በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ በእ​ና​ን​ተም ላይ በደ​ልሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፤ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 10:16
14 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንስ በድዬአለሁ፤ እግዚአብሔር እውነተኛ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን በደለኞች ነን።


“ንጹሑን ሰው ለሞት አሳልፌ በመስጠቴ በድዬአለሁ።” እነርሱ ግን “ታዲያ፥ እኛ ምን ቸገረን! የራስህ ጉዳይ ነው!” አሉት።


ኃጢአቱን የሚደብቅ ኑሮው አይሳካለትም፤ ኃጢአቱን ተናዝዞ ዳግመኛ ኃጢአት ከመሥራት የሚቈጠብ ግን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛል።


ጌታዬ ሆይ! ኃጢአት እንደ ሠራሁ ዐውቃለሁ፤ ዛሬ ግን ከሰሜን የእስራኤል ነገዶች የመጀመሪያው በመሆን አንተን ለመቀበል መጥቼአለሁ።”


ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።


ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።


ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አዎ፤ እኔ ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና አንተ የሰጠኸኝን መመሪያ አልጠበቅሁም፤ ወታደሮቼን በመፍራት እነርሱ የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤


በለዓምም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በእርግጥ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ አንተ እኔን ለመቃወም በመንገድ ላይ መቆምህን አላወቅሁም ነበር፤ አሁንም ወደዚያ መሄዴ ስሕተት መስሎ ከታየህ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።”


ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው፥ “በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ክፉ ቃል በመናገራችን በድለናል፤ አሁንም እነዚህ ተናዳፊ እባቦች ከእኛ እንዲወገዱ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን” አሉት፤ ሙሴም ለሕዝቡ ጸለየ።


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።


ከዚህ በኋላ ንጉሡ ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ሄዳችሁ በዚህች አገር ውስጥ ለአምላካችሁ መሥዋዕት አቅርቡ” አላቸው።


ነገር ግን ዳዊት ሕዝቡን ከቈጠረ በኋላ የኅሊና ወቀሳ ስላስጨነቀው እግዚአብሔርን “እኔ ይህን በማድረጌ ታላቅ በደል ፈጽሜአለሁ፤ የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራሁም እባክህ ይቅር በለኝ!” ሲል ለመነ።


ዳዊትም ሕዝቡን ይቀሥፍ የነበረውን መልአክ አይቶ እግዚአብሔርን “በደል የፈጸምኩት እኔ ነኝ፤ እኔም ራሴ ክፉ ነገርን አደረግሁ፤ ታዲያ ይህ ምስኪን ሕዝብ ምን በደለህ? ይህ መቅሠፍት በእርሱ ላይ ከሚወርድ ይልቅ በእኔና በቤተሰቤ ላይ ይሁን” ሲል ጠየቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios