ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።
2 ነገሥት 19:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀደሙት አባቶቼ ያጠፏቸውን፣ የጎዛንን፣ የካራንን፣ የራፊስን እንዲሁም በተላሳር የሚኖሩ የዔድንን ሰዎች የአሕዛብ አማልክት አድነዋቸዋልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዳንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቶች ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፌስን በታኤሴቴም የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን? |
ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።
ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ፑል ወይም ቲግላት ፐሌሴር ተብሎ የሚጠራውን የአሦርን ንጉሠ ነገሥት አነሣሥቶ ምድራቸውን እንዲወር አደረገ፤ በዚህ ዐይነት ቲግላት ፐሌሴር የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ በኩል ያለውን የምናሴን ነገድ እኩሌታ ማርኮ በመውሰድ በሐላሕ፥ በሐቦርና በሃራ እንዲሁም በጎዛን ወንዝ ዳርቻ እንዲኖሩ አደረጋቸው እስከ ዛሬም ድረስ በዚያው ይገኛሉ።
የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር ይኖሩ የነበሩትን የዔደንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንዳቸው እንኳ ሊያድኑአቸው ችለዋልን?
በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ አባቱ ከሞተ በኋላም እግዚአብሔር ከካራን አውጥቶ ዛሬ እናንተ ወደምትኖሩባት አገር አመጣው።