Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዳንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቀደሙት አባቶቼ ያጠፏቸውን፣ የጎዛንን፣ የካራንን፣ የራፊስን እንዲሁም በተላሳር የሚኖሩ የዔድንን ሰዎች የአሕዛብ አማልክት አድነዋቸዋልን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ ጎዛ​ንን፥ ካራ​ንን፥ ራፌ​ስን በታ​ኤ​ሴ​ቴም የነ​በ​ሩ​ት​ንም የዔ​ድ​ንን ልጆች፥ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 19:12
11 Referencias Cruzadas  

ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።


የታራም ዕድሜ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ሆነ፥ ታራም በካራን ሞተ።


ጌታ እግዚአብሔርም፥ በስተ ምሥራቅ፥ በዔድን ገነትን ተከለ፤ የፈጠረውንም ሰው ከዚያ አኖረው።


ያዕቆብም፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ?” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛ የካራን ነን” አሉት።


ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?


የእስራኤልም አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፎሐን መንፈስ፥ የአሦርንም ንጉሥ የቴልጌል-ቴልፌልሶርን መንፈስ አስነሣ፤ የሮቤልንና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ አፈለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳሉበት ወደ አላሔና ወደ አቦር፥ ወደ ሃራና ወደ ጎዛን ወንዝ አመጣቸው።


አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፍስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸው?


ሐራን፥ ካኔ፥ ዔድን፥ የሳባ ነጋዴዎች፥ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ ነበሩ።


በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ እናንተ ዛሬ ወደምትኖሩባት ወደዚች አገር አወጣው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos