Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 19:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን፥ ጎዛ​ንን፥ ካራ​ንን፥ ራፌ​ስን በታ​ኤ​ሴ​ቴም የነ​በ​ሩ​ት​ንም የዔ​ድ​ንን ልጆች፥ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቀደሙት አባቶቼ ያጠፏቸውን፣ የጎዛንን፣ የካራንን፣ የራፊስን እንዲሁም በተላሳር የሚኖሩ የዔድንን ሰዎች የአሕዛብ አማልክት አድነዋቸዋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዳንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን፥ ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፊስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች፥ የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 19:12
11 Referencias Cruzadas  

በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


የካ​ራ​ንና የካኔ፥ የኤ​ደ​ንም ሰዎች ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ አሦ​ርና ኪል​ማ​ድም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ።


ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?


ከዚ​ህም በኋላ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሀገር ወጥቶ በካ​ራን ተቀ​መጠ፤ ከዚ​ያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እና​ንተ ወደ አላ​ች​ሁ​ባት ወደ​ዚች ሀገር አመ​ጣው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ የፋ​ሎ​ክን መን​ፈስ፥ የአ​ሦ​ር​ንም ንጉሥ የቴ​ል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶ​ርን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ የሮ​ቤ​ል​ንና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ አፈ​ለሰ፥ እስከ ዛሬም ወዳ​ሉ​በት ወደ አላ​ሔና ወደ ኦቦር፥ ወደ ሃራ​ንና ወደ ጎዛን ወንዝ አመ​ጣ​ቸው።


ያዕ​ቆ​ብም፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ንት ከወ​ዴት ናችሁ?” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም በኤ​ዶም በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ ገነ​ትን ተከለ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም ሰው በዚያ አኖ​ረው።


እነሆ፥ የአ​ሦር ነገ​ሥ​ታት በም​ድር ሁሉ ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን፥ እን​ዴ​ትስ እን​ዳ​ጠ​ፉ​አ​ቸው ሰም​ተ​ሃል፤ አን​ተስ ትድ​ና​ለ​ህን?


ታራም በካ​ራን ምድር የኖ​ረ​በት ዘመን ሁለት መቶ አም​ስት ዓመት ሆነ፤ ታራም በካ​ራን ሞተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios