Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 37:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር ይኖሩ የነበሩትን የዔደንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንዳቸው እንኳ ሊያድኑአቸው ችለዋልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የቀደሙት አባቶቼ ያጠፏቸውን፣ የጎዛንን፣ የካራንን፣ የራፊስን እንዲሁም በተላሳር የሚኖሩ የዔድንን ሰዎች የአሕዛብ አማልክት አድነዋቸዋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፥ ካራንን፥ ራፍስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አባ​ቶች ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ውን በቴ​ማን ያሉ​ትን ጎዛ​ን​ንና ካራ​ንን፥ ራፌ​ስ​ንም የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት አዳ​ኑ​አ​ቸ​ውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን ካራንን፥ ራፍስን፥ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 37:12
19 Referencias Cruzadas  

ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።


ታራ 205 ዓመት ሲሆነው በካራን ሞተ።


ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ በእርግጥም ግብጻውያን የአብራም ሚስት በጣም ቈንጆ እንደ ሆነች አዩ።


እግዚአብሔር አምላክ በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ቦታን አዘጋጀ፤ የፈጠረውንም ሰው በዚያ እንዲኖር አደረገው።


ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤


ያዕቆብም እረኞቹን “ወዳጆቼ ሆይ፥ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ከካራን ነው” አሉት።


ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ ሌሎቹ ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዔዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?


ስለዚህ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔር ታደጋችኋል!’ እያለ በማሳሳት አያሞኛችሁ፤ ለመሆኑ ከሌሎች ሕዝቦች አማልክት መካከል አንድ እንኳ ከአሦር ንጉሥ እጅ አገሩን ለማዳን የቻለ ይገኛልን?


ታዲያ ይህ ከሆነ የሀማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም አማልክትስ የት ደረሱ? ለመሆኑ ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ሊያድን ችሎአልን?


የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከእኔ እጅ አገራቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”


የሐማት፥ የአርፋድ፥ የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት አሁን ወዴት አሉ?”


የካራን፥ የካኔህና የዔደን ከተሞች፥ የሳባ ነጋዴዎች፥ የአሹርና የኪልማድ ከተሞች፥ እነዚህ ሁሉ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።


የእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ በሆነችው በዔደን ውስጥ ትኖር ነበር፤ ሰርድዮን፥ ዐልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያሰጲድ፥ ሰንፔርና በሉር ተብለው በሚጠሩ የከበሩ ድንጋዮች ያጌጠ የወርቅ ልብስ ትለብስ ነበር፤ ከተፈጠርክበት ጊዜ አንሥቶ ይህ ሁሉ ነበረህ።


የደማስቆን ከተማ የቅጽር በር መዝጊያ ሁሉ እሰባብራለሁ፤ በአዌን ሸለቆ የሚኖሩትን ሕዝቦችና የቤትዔደንን መሪ አስወግዳለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርከው ወደ ቂር ይወሰዳሉ።”


እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos