Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 29:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ያዕቆብም እረኞቹን “ወዳጆቼ ሆይ፥ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ከካራን ነው” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ያዕቆብም እረኞቹን፣ “ወንድሞቼ፤ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “ከካራን ነን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ያዕቆብም፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ?” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛ የካራን ነን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ያዕ​ቆ​ብም፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ንት ከወ​ዴት ናችሁ?” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ያዕቆብም፦ ወንድሞቼ ሆይ እናንት የወዴት ናችሁ? አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 29:4
7 Referencias Cruzadas  

ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።


የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዐሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።


አሁንም ልጄ ሆይ፥ የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚኖረው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤


ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤


መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጒድጓዱ ውሃ ያጠጡአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩን መልሰው በጒድጓዱ አፍ ላይ ይከድኑታል።


እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና


በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ አባቱ ከሞተ በኋላም እግዚአብሔር ከካራን አውጥቶ ዛሬ እናንተ ወደምትኖሩባት አገር አመጣው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos