2 ቆሮንቶስ 5:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሥጋ ተለይተን ከጌታ ጋራ መኖርን እንደምንመርጥ ርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዎ፥ ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በጌታ ዘንድ መኖር እንመርጣለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታምነናል፤ ይልቁንም ከሥጋችን ተለይተን ወደ ጌታችን እንሄዳለንና ደስ ይለናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል። |
ጌታውም ‘መልካም አደረግህ፤ አንተ ታማኝና ደግ አገልጋይ! በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
ጌታውም ‘መልካም ነው! አንተ ታማኝና መልካም አገልጋይ በጥቂት ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ በብዙ ነገር ላይ እሾምሃለሁ፤ ና የጌታህን ደስታ ለመካፈል ግባ!’ አለው።
“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።
ጳውሎስ ግን “እንደዚህ እያለቀሳችሁ ስለምን ልቤን በሐዘን ትሰብሩታላችሁ? እኔ ስለ ጌታ ኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመታሰር ብቻ ሳይሆን ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” ሲል መለሰ።
ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።