2 ቆሮንቶስ 12:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ ታላቅ መገለጥ የተነሣ እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፣ እርሱም የሚያሠቃየኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚህን ግልጠት ልዩ ጸባይ በማየት እንዳልታበይ፥ ሥጋዬን መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ቢሆን በብዙ ራእይ እንዳልታበይ ሰውነቴን የሚወጋ እርሱም የሚጐስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው። |
ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
ነገር ግን የባቢሎን መልእክተኞች በአገሪቱ ስለ ተደረገው አስደናቂ ነገር ሊጠይቁት ወደ እርሱ መጥተው በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር በሕዝቅያስ ልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ለማወቅ ይፈትነው ዘንድ ተወው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በንቀት ከሚመለከትዋት፥ በዙሪያዋ ካሉ አገሮች ሁሉ እንደ እሾኽና አሜከላ በመሆን እስራኤልን የሚጐዳ ከእንግዲህ ወዲህ ማንም አይኖርም። እኔም ልዑል እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”
በምድሪቱ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ አሳዳችሁ ካላጠፋችሁ ግን ያስቀራችኋቸው ለዐይናችሁ እንደ ስንጥር ለጐናችሁም እንደ እሾኽ በመሆን ያስቸግሩአችኋል፤ በምትቀመጡባትም ምድር ዘወትር ጦርነት በማስነሣት ያስጨንቁአችኋል።
እነሆ፥ የአብርሃም ዘር የሆነች ይህች ሴት ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ በሰይጣን ታስራ ስትሠቃይ ኖራለች፤ ታዲያ፥ እርስዋ ታስራ ከምትሠቃይበት በሽታ በሰንበት ቀን መፈታት አይገባትምን?”
በኃጢአት የተሞላው የዚህ ሰው ሥጋ ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል። ይህንንም የምታደርጉት ጌታ ኢየሱስ ለፍርድ በሚመጣበት ቀን የዚህ ሰው ነፍስ እንድትድን ነው።
ምናልባት አንዳንዶች “የጳውሎስ መልእክቶች ከባዶችና ብርቱዎች ናቸው፤ እርሱ ራሱ ከእኛ ጋር ሲሆን ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይሉ ይሆናል።
እግዚአብሔርን በማወቅ ላይ እንቅፋት ሆነው የሚነሡትን ክርክርና ትዕቢት እናፈርሳለን፤ የሰውን ሐሳብ ሁሉ እየማረክንም ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።
እንዲሁም ማንም እንደ ባሪያ ቢያደርጋችሁ፥ ማንም ቢበዘብዛችሁ፥ ማንም ቢጠቀምባችሁ፥ ማንም ቢንቃችሁ፥ ማንም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሣላችሁ።
ራሱንም ከወገኖቹ ከእስራኤላውያን እበልጣለሁ ብሎ እንዳይታበይና ከእግዚአብሔርም ትእዛዞች እንዳይርቅ ይጠብቀዋል። ይህን ቢያደርግ ለብዙ ዘመን ይነግሣል፤ ልጆቹም በእስራኤል ላይ ለብዙ ዘመን ይነግሣሉ።
ስለዚህ አሁን እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ እንደማላስወጣቸው እነግራችኋለሁ፤ እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ይሆናሉ፤ ባዕዳን አማልክታቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል።”