Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔርም ሰይጣንን “መልካም ነው፤ አትግደለው እንጂ በእርሱ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታም ሰይጣንን፦ “ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “እነሆ፥ ሥጋ​ው​ንና አጥ​ን​ቱን በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ። ነገር ግን ሕይ​ወ​ቱን ተው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔም ሰይጣንን፦ ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው አለው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 2:6
15 Referencias Cruzadas  

መልአኩም ‘ሄጄ የአክዓብ ነቢያት ሁሉ ሐሰት እንዲናገሩ አደርጋለሁ’ ሲል መለሰ፤ እግዚአብሔርም ‘እንግዲያውስ ሄደህ አሳስተው፤ ይከናወንልሃል’ አለው።”


ነገር ግን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ብታጠፋበት ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”


እግዚአብሔርም ሰይጣንን “እሺ፤ እንግዲያውስ በኢዮብ ላይ ብቻ አንዳች ጒዳት አታድርስበት እንጂ ባለው ሀብት ሁሉ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ” አለው። ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።


ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ በመላ ሰውነቱ ላይ ጒዳት ብታደርስበት በእርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል!” አለው።


ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ኢዮብን ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ በከባድ ቊስል እንዲሠቃይ አደረገው።


ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።


ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት ይበልጣል።


በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ሌላ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ፈተና እንዲደርስባችሁ አይፈቅድም፤ በምትፈተኑበትም ጊዜ የምትታገሡበትን ኀይል በመስጠት ከፈተናው የምትወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላችኋል።


ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።


ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።


ሺህ ዓመት ከተፈጸመ በኋላ ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos