2 ቆሮንቶስ 12:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን ስለ እናንተ ያለኝን ሁሉ ራሴንም ጭምር ብሰጥ ደስ ይለኛል፤ ታዲያ እኔ የምወድዳችሁ ይህን ያህል ከሆነ፣ እናንተ የምትወድዱኝ በጥቂቱ ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን አወጣለሁ፤ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ፥ የናንተ ፍቅር እንዴት ያንሳል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወጣለሁ፤ ስለ ሕይወታችሁም ሰውነቴን አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እናንተንም እጅግ ብወዳችሁ ራሴን ወደድሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን እከፍላለሁ፥ ራሴን እንኳ እከፍላለሁ። ከመጠን ይልቅ ብወዳችሁ በዚህ ልክ ፍቅራችሁ የሚያንስ ነውን? |
ንጉሡም እጅግ አዘነ፤ በቅጽር በሩ አናት ላይ ወደሚገኘውም ክፍል ወጥቶ አለቀሰ፤ ወደዚያም ሲመጣ “ልጄ ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! አቤሴሎም ልጄ! ምነው በአንተ ምትክ እኔ በሞትኩ ልጄ ሆይ! አቤሴሎም ልጄ!” እያለ በመጮኽ ያለቅስ ነበር።
አሁን ስለ እኛ የምታውቁት በከፊል ነው፤ በኋላ ግን በሙላት እንደምታስተውሉት ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚህም ምክንያት ጌታ ኢየሱስ በሚመጣበት ቀን እኛ በእናንተ እንደምንመካ እናንተም በእኛ ትመካላችሁ።
እኛ መከራ ስንቀበል እናንተ መጽናናትንና መዳንን ታገኛላችሁ፤ እኛ ስንጽናና ደግሞ እናንተም እኛ የምንቀበለውን ዐይነት መከራ በትዕግሥት ተቀብላችሁ ትጽናናላችሁ፤
ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ አሁን ሦስተኛዬ ጊዜዬ ነው፤ እኔ ሸክም ልሆንባችሁ አልፈልግም፤ እኔ የምፈልገው እናንተን እንጂ ገንዘባችሁን አይደለም። ለልጆቻቸው ሀብት ማከማቸት የሚገባቸው ወላጆች ናቸው እንጂ ልጆች ለወላጆቻቸው ሀብት አያከማቹም።
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
እንደዚያ የጻፍኩላችሁም ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ብዬ ነው፤ የእኔ ደስታ የሁላችሁም ደስታ መሆኑን አምናለሁ።
ይህንንም የምለው በእናንተ ላይ ለመፍረድ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኳችሁ እናንተ በልባችን ውስጥ ናችሁ፤ ስለዚህ በሕይወትም ሆነ በሞት ሁልጊዜ ከእናንተ አንለይም።
ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት ተጨማሪ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል፤ እናንተም የደስታዬ ተካፋዮች ትሆናላችሁ።
አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል፤ አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጐደለብኝን በሥጋዬ አሟላለሁ።
ስለዚህ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘውን መዳንና ዘለዓለማዊ ክብርን እንዲያገኙ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሰዎች ስል ሁሉን ነገር እታገሣለሁ።
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ በሥልጣናቸውም ሥር ሁኑ፤ እነርሱ የሚጠየቁበት ኀላፊነት ስላለባቸው ስለ ነፍሳችሁ ጉዳይ ይተጋሉ፤ እናንተ ብትታዘዙአቸው እነርሱ ሥራቸውን በደስታ ያከናውናሉ፤ ያለበለዚያ ሥራቸውን በሐዘን ይሠራሉ፤ ይህም እናንተን የሚጠቅም አይሆንም።