Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 11:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ምክንያቱስ ምንድን ነው? ስለማልወዳችሁ ነውን? እንደምወዳችሁስ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህን የምለው ለምንድን ነው? ስለማልወድዳችሁ ነውን? እንደምወድዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ምን ነው? አል​ወ​ዳ​ች​ሁ​ምና ነውን? እን​ደ​ም​ወ​ድ​ዳ​ች​ሁስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለ ምን? ስለማልወዳችሁ ነውን? እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 11:11
15 Referencias Cruzadas  

ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?


ይህንንም የምለው በእናንተ ላይ ለመፍረድ አይደለም። ከዚህ በፊት እንደ ነገርኳችሁ እናንተ በልባችን ውስጥ ናችሁ፤ ስለዚህ በሕይወትም ሆነ በሞት ሁልጊዜ ከእናንተ አንለይም።


ልጆችዋንም በሞት እቀጣለሁ፤ አብያተ ክርስቲያንም ሁሉ የሰውን ሐሳብና ምኞት የምመረምር እኔ መሆኔን ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደየሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።


ለዘለዓለም የተመሰገነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንደማልዋሽ ያውቃል።


የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ፥ መንፈስ ቅዱስን ለእኛ እንደ ሰጠው ዐይነት ለእነርሱም በመስጠት መሰከረላቸው።


ሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፥ እኔ እንደምወድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ “በጎቼን አሰማራ፤


አንተ የተሰወረውን ሐሳባችንን ስለምታውቅ በደላችንን ገልጠህ ባየህብን ነበር።


“ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤


የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ በመኖሩ እንዳልመካ የሚያደርገኝ በአካይያ አገሮች ማንም የለም።


ዘወትር በጸሎቴ እንደማስባችሁ፥ ስለ ልጁ የሚናገረውን ወንጌል በማስተማር በሙሉ ልቤ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።


እኛ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ንግድ ዕቃ እንደሚቸረችሩት እንደ ብዙዎቹ አይደለንም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንደ ተላኩ ቅን መልእክተኞች በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios