Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ስለዚህ እኛ መላልሰን ለሞት ስንጋለጥ እናንተ ግን ለሕይወት ትጋለጣላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለዚህ ሞት በእኛ፥ ሕይወት ግን በእናንተ ይሠራል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 4:12
9 Referencias Cruzadas  

እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ግን ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናል፤ የእኛ ጸሎት እናንተ ፍጹሞች እንድትሆኑ ነው።


ፍቅር ምን እንደ ሆነ የምናውቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ስለ ሰጠን ነው፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።


እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል።


የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።


ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት ተጨማሪ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል፤ እናንተም የደስታዬ ተካፋዮች ትሆናላችሁ።


ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?


እናንተ በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን ርዳታ እርሱ ለማሟላት ብሎ ስለ ክርስቶስ ሥራ ለሕይወቱ ሳይሳሳ ለሞት ተቃርቦ ነበር።


የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን።


ይሁን እንጂ “አመንኩ፤ ስለዚህ ተናገርኩ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ እኛም ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios