በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
2 ቆሮንቶስ 1:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምሕረት አባትና መጽናናትን ሁሉ ለሚሰጥ እንዲሁም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለእግዚአብሔር፥ ምስጋና ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምሕረት አባት፥ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። |
በጠላቶችህ ላይ ድልን ያቀዳጀህ፥ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።” አብራምም በምርኮ ካገኘው ሀብት ሁሉ አንድ ዐሥረኛውን ለመልከ ጼዴቅ ሰጠው።
እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!
ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው።
“ከእናቴ ማሕፀን ራቁቴን ተወለድኩ፤ ስሞትም ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን!” አለ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከመቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ እጅግ ያስፈራል፤ እርሱ ለሕዝቡ ብርታትንና ኀይልን ይሰጣል። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።
ክብር የሚገባው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን በይበልጥ ታውቁ ዘንድ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤
በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የማይኖርና ከእርሱም ርቆ የሚሄድ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የለም፤ በክርስቶስ ትምህርት ጸንቶ የሚኖር ሰው ግን አብና ወልድ ከእርሱ ጋር አሉ።