Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 11:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ለዘለዓለም የተመሰገነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እንደማልዋሽ ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ የኢየሱስ አምላክና አባት እንደማልዋሽ ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ለዘለዓለም የተባረከ አምላክ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እንዳልዋሸሁ ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 11:31
22 Referencias Cruzadas  

ኢያሱ፥ ቃድሚኤል፥ ባኒ፥ ሐሸባንያ፥ ሼሬብያ፥ ሆዲያ፥ ሸባንያና ፐታሕያ ተብለው የሚጠሩት ሌዋውያን፦ “ተነሥታችሁ በመቆም ዘለዓለማዊውን አምላካችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ከምስጋናና ከበረከት ሁሉ በላይ፥ ከፍ ከፍ ይበል! በሉ” አሉአቸው።


ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን! አሜን! አሜን!


እኔና አብ አንድ ነን።”


ኢየሱስ “ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሂጂና ‘እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፥ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዐርጋለሁ ብሎአል’ ብለሽ ንገሪያቸው” አላት።


ይህም የሆነው የእግዚአብሔርን እውነት በሐሰት ስለ ለወጡ፥ በፈጣሪ ፈንታ ፍጡርን ስላመለኩና ስለ አገለገሉ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ለዘለዓለም የተመሰገነ ነው፤ አሜን።


ዘወትር በጸሎቴ እንደማስባችሁ፥ ስለ ልጁ የሚናገረውን ወንጌል በማስተማር በሙሉ ልቤ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።


እንዲሁም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር በአንድ ልብና በአንድ ቃል እንድታከብሩት ያድርጋችሁ።


በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ኅሊናዬም እንደማልዋሽ ይመሰክርልኛል።


እነርሱ በትውልዳቸው ከነገድ አባቶች የመጡ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የመጣው ከእነርሱ ዘር ነው፤ እርሱ ከሁሉ በላይ ነው፤ ለዘለዓለምም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን!


እኔ ወደ ቆሮንቶስ ተመልሼ ያልመጣሁበት ምክንያት እናንተን እንዳላሳዝናችሁ ለእናንተ በመራራት ነው፤ ለዚሁም እግዚአብሔር ምስክሬ ነው፤


ለምሕረት አባትና መጽናናትን ሁሉ ለሚሰጥ እንዲሁም ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አባት ለእግዚአብሔር፥ ምስጋና ይሁን።


ምክንያቱስ ምንድን ነው? ስለማልወዳችሁ ነውን? እንደምወዳችሁስ እግዚአብሔር ያውቃል።


ይህ የምጽፍላችሁ ሐሰት እንዳልሆነ በእግዚአብሔር ፊት አረጋግጥላችኋለሁ።


በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።


እንግዲህ በእግዚአብሔር አብ ፊት በጒልበቴ ተንበርክኬ የምጸልየው በዚህ ምክንያት ነው።


ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ዘወትር እናመሰግናለን።


አንድም ጊዜ በቃላት በማቈላመጥ ወይም የገንዘብ ፍላጎት ኖሮን ከቶ እንዳልተናገርን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክራችን ነው።


እውነተኛው ትምህርት ግን የሚገኘው ስለተመሰገነው እግዚአብሔር ከሚያበሥረው ክቡር ወንጌል ነው፤ ይህም ወንጌል ለእኔ በዐደራ የተሰጠኝ ነው።


ስለዚህ ለዘለዓለማዊው ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ለአንዱ አምላክ ክብርና ምስጋና ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ እርሱን ከቶ ማንም አላየውም፤ ማንም ሊያየውም አይችልም፤ ክብርና ዘለዓለማዊ ኀይል ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ምክንያት ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ በታላቅ ምሕረቱ በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos