ከዚህ በኋላ ዳዊት ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንድዋ ልውጣን? ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወደ የትኛይቱ ከተማ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ወደ ኬብሮን ከተማ ሂድ” አለው።
1 ሳሙኤል 23:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት “ሄጄ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን?” ሲል የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ! በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ በመጣል ቀዒላን ከጥፋት አድን” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “እነዚህን ፍልስኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም፥ “ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያንን ልምታን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቂአላንም አድን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ልሂድን? እነዚህንስ ፍልስጥኤማውያን ልምታን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ሂድ፥ ፍልስጥኤማውያንን ምታ ቅዒላንም አድን አለው። |
ከዚህ በኋላ ዳዊት ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንድዋ ልውጣን? ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወደ የትኛይቱ ከተማ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ወደ ኬብሮን ከተማ ሂድ” አለው።
ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ልጣልባቸውን? ድልንስ ትሰጠኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ በእነርሱ ላይ አደጋ ጣልባቸው! እኔ በእነርሱ ላይ ድልን እሰጥሃለሁ!” ሲል መለሰለት።
ዳዊትም እንደገና እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰለት “አሁን ካለህበት በኩል በእነርሱ ላይ አደጋ አትጣል፤ ነገር ግን ከወዲያ በኩል በስተ ኋላ በመዞር ከሾላ ዛፎች ፊት ለፊት ሆነህ በእነርሱ ላይ አደጋ ለመጣል ተዘጋጅ።
ዳዊትም “በፍልስጥኤማውያን ላይ ጦርነት ልክፈትን? በእነርሱስ ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ፥ አደጋ ጣልባቸው! እኔም ድልን አጐናጽፍሃለሁ!” አለው።
ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።”
ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ “በከነዓናውያን ላይ አደጋ ለመጣል ከነገዶቻችን መካከል ተቀዳሚ ሆኖ ማን ይዝመት?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ።
ስለዚህም እነርሱ “ሌላ የቀረ ይኖር ይሆን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “ሳኦል እነሆ በዕቃ መካከል ተደብቆ ይገኛል” ሲል መለሰላቸው።
ሳኦልም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ እንጣልባቸውን? ድልንስ ለእኛ ትሰጣለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ቀን ምንም መልስ አልሰጠም።
ነገር ግን የዳዊት ተከታዮች “በዚህ በይሁዳ ስንኖር የምንፈራው ብዙ ነገር አለ፤ አሁን ደግሞ ወደ ቀዒላ ሄደን በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ አደጋ ብንጥል ችግራችን የባሰ ችግር ይገጥመናል!” አሉት።
ከዚህም የተነሣ ዳዊት እንደገና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም “እኔ በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ስለማቀዳጅህ ሄደህ በቀዒላ ላይ አደጋ ጣል” አለው።
ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።