1 ሳሙኤል 22:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ሳኦል በአጠገቡ ወደቆሙት ዘብ ጠባቂዎች መለስ ብሎ “እነዚህን የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሉ! እነርሱ ከዳዊት ጋር በእኔ ላይ ዐምፀውብኛል፤ እንዲሁም ሁሉን ነገር እያወቁ ዳዊት መኰብለሉን እንኳ አልነገሩኝም” አላቸው፤ ዘብ ጠባቂዎቹ ግን “የእግዚአብሔርን ካህናት አንገድልም” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ በአጠገቡ የቆሙትን ዘቦች፣ “እነዚህም የእግዚአብሔር ካህናት ከዳዊት ጋራ ስላበሩ፣ ዳዊት መኰብለሉንም እያወቁ ስላልነገሩኝ ዙሩና ግደሏቸው” ሲል አዘዛቸው። የንጉሡ ሹማምት ግን እጃቸውን አንሥተው የእግዚአብሔርን ካህናት ለመምታት ፈቃደኞች አልሆኑም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ንጉሡ በአጠገቡ የቆሙትን ዘቦች፥ “እነዚህም የጌታ ካህናት ከዳዊት ጋር ስላበሩ፥ ዳዊት መኰብለሉንም እያወቁ ስላልነገሩኝ ዞራችሁ ግደሏቸው” ሲል አዘዛቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን እጃቸውን አንሥተው የጌታን ካህናት ለመምታት ፈቃደኞች አልሆኑም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን እግረኞች፥ “የእግዚአብሔር ካህናት እጅ ከዳዊት ጋር ነውና፥ ኵብለላውንም ሲያውቁ አልነገሩኝምና፥ ዞራችሁ ግደሉአቸው” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን እጃቸውን በእግዚአብሔር ካህናት ላይ ይዘረጉ ዘንድ እንቢ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን እግረኞች፦ የእግዚአብሔር ካህናት እጅ ከዳዊት ጋር ነውና፥ ኵብለላውንም ሲያውቁ በጆሮዬ አልገለጡምና ዞራችሁ ግደሉአቸው አላቸው። የንጉሡ ባሪያዎች ግን እጃቸውን በእግዚአብሔር ካህናት ላይ ይዘረጉ ዘንድ እንቢ አሉ። |
ከአቤሴሎም በኋላ ከዳዊትና ከሐጊት የተወለደ በሕይወት ያለ ተከታይ ልጅ አዶንያስ ነበር፤ እርሱም እጅግ መልከ ቀና ነበር፤ ዳዊት ስለማናቸውም ነገር ምክርና ተግሣጽ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አዶንያስ ለመንገሥ ፈለገ፤ ይህንንም ፍላጎቱን ለማሟላት ሠረገሎችን፥ ፈረሶችንና ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ።
እነርሱንም ለመተካት ንጉሥ ሮብዓም ጋሻዎችን ከነሐስ አሠርቶ የቤተ መንግሥቱን ቅጽር በር የመጠበቅ ኀላፊነት ባላቸው የዘብ አለቆች እንዲጠበቁ አደረገ፤
ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረችበትም ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ፥ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ ይመግባቸው ነበር።
ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለዘብ ጠባቂዎችና ለጦር መኰንኖች “ገብታችሁ እነዚህን ሁሉ ግደሉ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ!” ሲል አዘዛቸው፤ እነርሱም ሰይፍ ሰይፋቸውን በመምዘዝ ገብተው ሁሉንም ገደሉ፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጐተቱ ወደ ውጪ አወጡት፤ ከዚህም በኋላ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገብተው፥
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።
ሕዝቡ ግን ሳኦልን “ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል ያስገኘ ዮናታን ይሞታልን? ከቶ አይደረግም! መሞቱ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም እንምላለን፤ ዛሬ እርሱ ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ረዳትነት የተፈጸመ ነው” አሉ፤ በዚህም ዐይነት ሕዝቡ ዮናታንን ከሞት ቅጣት አዳኑት።
እነሆ፥ ከአንተ ቤተሰብ መካከል አንድም ሰው ወደ ሽምግልና ዕድሜ እንዳይደርስ አንተንና የአባቶችህን ቤተሰብ የማጠፋበት ጊዜ እየተቃረበ ነው።
ከዚህም የተነሣ ዮናታንን ለመግደል የያዘውን ጦር ወረወረበት፤ ስለዚህም ዮናታን አባቱ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቊርጥ ውሳኔ ማድረጉን አረጋገጠ፤
ሳኦልም “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ስለምንድን ነው? ለእርሱ ምግብና ሰይፍ ሰጥተኸዋል እግዚአብሔርንም ጠይቀህለታል፤ እነሆ፥ እርሱ አሁን በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶ እኔን ለመግደል አጋጣሚ ጊዜ በመፈለግ ላይ ነው” ሲል ጠየቀው።
እባክሽን ይህን ጉዳይ አስቢበትና ማድረግ ስለሚገባሽ ነገር ወስኚ፤ አለበለዚያ ለጌታችንና ለቤተሰቡ ሁሉ አደገኛ ጥፋት ይሆናል፤ እርሱ እንደ ሆነ የማንንም ምክር የማይሰማ ደረቅ ሰው ነው!”
እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤