1 ነገሥት 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5-6 ከአቤሴሎም በኋላ ከዳዊትና ከሐጊት የተወለደ በሕይወት ያለ ተከታይ ልጅ አዶንያስ ነበር፤ እርሱም እጅግ መልከ ቀና ነበር፤ ዳዊት ስለማናቸውም ነገር ምክርና ተግሣጽ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አዶንያስ ለመንገሥ ፈለገ፤ ይህንንም ፍላጎቱን ለማሟላት ሠረገሎችን፥ ፈረሶችንና ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 በዚህ ጊዜ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ “እነግሣለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ስለዚህ ሠረገሎችንና ፈረሶችን እንዲሁም ከፊት ከፊቱ የሚሄዱ ዐምሳ ሰዎችን አዘጋጀ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ያንጊዜ የሐጊት ልጅ አዶንያስ፦ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣሣ፤ ለራሱም ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን፥ እንዲሁም ኀምሳ ጋሻ ጃግሬዎችን አዘጋጀ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የአጊትም ልጅ አዶንያስ፥ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎችን አዘጋጀ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የአጊትም ልጅ አዶንያስ “ንጉሥ እሆናለሁ፤” ብሎ ተነሣ፤ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎች አዘጋጀ። Ver Capítulo |