በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።
1 ሳሙኤል 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎችን ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱም ሺህ በማኪማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፤ አንዱም ሺህ በብንያም ገባዖን ከልጁ ከዮናታን ጋር ነበሩ፤ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱን ወደ ድንኳኑ አሰናበተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፥ ሁለቱም ሺህ በማክማስና በቤቴል ተራራ ከሳኦል ጋር ነበሩ፥ አንዱም ሺህ በብንያም ጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ፥ የቀረውንም ሕዝብ እያንዳንዱ ወደ ድንኳኑ አሰናበተ። |
በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ጼላዕ፥ ኤሌፍ፥ ኢያቡስ (ኢየሩሳሌም) ጊብዓና ቂርያትይዓሪም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙትን ትናንሽ ከተሞችንም ይጨምራሉ። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየወገኖቻቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው።
ከዚያም አልፈህ የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ወደሚገኝበት ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ ወደ ከተማይቱም መግቢያ በር በምትደርስበትም ጊዜ በኮረብታው ላይ መሥዋዕት አቅርበው የሚመለሱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ፤ እነርሱም በገና እየደረደሩ፥ ከበሮ እየመቱ፥ ዋሽንት እየነፉ፥ በመሰንቆ ዜማ ሲዘምሩና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ትንቢት ሲናገሩ ታገኛቸዋለህ።
ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሕዝቡ ሊከዱኝ ተቃርበው ነበር፤ አንተም በቀጠርከኝ ሰዓት ሳትመጣ ቀረህ፤ ከዚህም በላይ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በሚክማስ ተሰለፉ፤
ሳሙኤልም ከጌልጌላ ተነሥቶ ሄደ፤ ሳኦልም ከወታደሮቹ ጋር ለመደባለቅ ሲሄድ የቀሩት ሰዎች ተከተሉት፤ ከጌልገላም ተነሥተው በብንያም ግዛት ወደምትገኘው ወደ ጊብዓ ሄዱ፤ ሳኦልም ሠራዊቱን በቈጠረ ጊዜ ብዛታቸው ስድስት መቶ ሆኖ ተገኘ፤
ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ መሸጉ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችም ምሽግ በሚክማስ ነበር፤
ፍልስጥኤማውያንም እስራኤላውያንን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ እነርሱም ከሠላሳ ሺህ የጦር ሠረገሎችና ከስድስት ሺህ ፈረሰኞች ጋር ብዛቱ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ነበራቸው፤ ሄደውም በቤትአዌን በስተምሥራቅ ሚክማስ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መሸጉ።
በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር።
ከአለቶቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር።
ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።
በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤
እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤