2 ሳሙኤል 21:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ከርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፣ “ዕሺ እሰጣችኋለሁ” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ከእርሱ ዘሮች ሰባት ወንዶች ልጆች ይሰጠን፤ እኛም ከጌታ በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ በጌታ ፊት እንስቀላቸው” ብለው መለሱለት። ስለዚህ ንጉሡ፥ “እሺ! እሰጣችኋለሁ” አለ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ከልጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል ሀገር በገባዖን ለእግዚአብሔር እንሠቅላቸዋለን።” ንጉሡም፥ “እሰጣችኋለሁ” አለ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ካሰበው ሰው ልጆች ሰባት ሰዎች አሳልፈህ ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ ለእግዚአብሔር እንሰቅላቸዋለን አሉት። ንጉሡም፦ እሰጣችኋለሁ አለ። Ver Capítulo |
እነርሱ የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የኢሸማዓ ልጆች በሆኑት በአሒዔዜርና በዮአሽ አመራር ሥር ነበሩ። የወታደሮቹም ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የዓዝማዌት ልጆች ይዚኤልና ፔሌጥ፥ የዐናቶት ተወላጆች የሆኑት በራካና ኢዩ፥ ዝነኛ ወታደር የነበረው፥ በኋላም የሠላሳዎቹ ኀያላን መሪዎች ከሆኑት አንዱ የሆነው፥ የገባዖን ተወላጅ ዩሽማዕያ፥ የገዴራ ተወላጆች የሆኑት ይርመያ፥ ያሕዚኤል፥ ዮሐናንና ዮዛባድ፥ የሐሪፍ ተወላጆች የሆኑት ኤልዑዛይ፥ ያሪሞት፥ በዓልያ፥ ሸማርያና ሸፋጥያ፥ ከቆሬ ጐሣዎች የሆኑት ኤልቃና፥ ዩሺያሁ፥ ዐዛርኤል፥ ዮዔዜርና ያሸብዓም፥ የገዶር ተወላጆች የሆኑት የይሮሐም ልጆች ዮዔላና ዘባድያ።