‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል’ ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያም በኋላ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”
1 ነገሥት 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎችም ኤልዛቤል ያዘዘቻቸውን አደረጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ በናቡቴ ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎችና መኳንንት በደብዳቤዎቹ ላይ ኤልዛቤል እንደ ጻፈችላቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ “በቃ፥ ለሰልፍ የሚታጠቅ ጋሻ ጦሩን እንደሚያወልቅ አይመካ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፥ “ይሁን፤ ይህ ጐባጣ እንደ ቀና አይመካ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፦ በቃ፤ ለሰልፍ የሚታጠቅ ጋሻ ጦሩን እንደሚያወልቅ አይመካ አለው። |
‘እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቦአል’ ብለው የሚናገሩ ሁለት የሐሰት ምስክሮችንም አቅርቡ፤ ከዚያም በኋላ ናቡቴን ከከተማው ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ በመውገር ግደሉት።”
ንጉሥ ኢዮአስ በዘካርያስ ላይ በተደረገው ሤራ ተባባሪ ሆነ፤ ሕዝቡም በንጉሡ ትእዛዝ ዘካርያስን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።
ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”
ከዚያ በኋላ ሄሮድስ፥ የከዋክብት ተመራማሪዎቹ እንዳታለሉት በተገነዘበ ጊዜ፥ በጣም ተቈጣ፤ ወደ ቤተልሔምና በዙሪያዋም ወዳሉት መንደሮች ሁሉ ወታደሮቹን ልኮ፥ ከከዋክብት ተመራማሪዎቹ በተረዳው ዘመን መሠረት፥ ዕድሜአቸው ሁለት ዓመት የሆናቸውንና ከዚያ በታች የሆኑትን በቤተልሔምና በአካባቢው የነበሩትን ወንዶች ሕፃናትን አስገደለ።
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።
ከዚህም በኋላ ሳኦል በአጠገቡ ወደቆሙት ዘብ ጠባቂዎች መለስ ብሎ “እነዚህን የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሉ! እነርሱ ከዳዊት ጋር በእኔ ላይ ዐምፀውብኛል፤ እንዲሁም ሁሉን ነገር እያወቁ ዳዊት መኰብለሉን እንኳ አልነገሩኝም” አላቸው፤ ዘብ ጠባቂዎቹ ግን “የእግዚአብሔርን ካህናት አንገድልም” አሉ።