Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 5:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያት ግን እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ “ለሰው ከመታዘዝ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባናል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ጴጥሮስና ሌሎች ሐዋርያትም መልሰው እንዲህ አሉ፤ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ “ከሰው ሥልጣን ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ጴጥ​ሮ​ስና ሐዋ​ር​ያ​ትም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “ለሰው ከመ​ታ​ዘዝ ይልቅ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዝ ይገ​ባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 5:29
10 Referencias Cruzadas  

አዳምንም እንዲህ አለው፥ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘አትብላ’ ያልኩህን ፍሬ ከዛፉ ወስደህ ስለ በላህ፥ አንተ በፈጸምከው ክፉ ሥራ ምክንያት ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህ ሁሉ ምግብህን ከእርስዋ የምትበላው በብርቱ ድካም ነው።


ንጉሡ ግን ኢዮአብና የጦር መኰንኖቹ ትእዛዙን እንዲፈጽሙ ስላስገደዳቸው ከፊቱ ወጥተው የእስራኤልን ሕዝብ ለመቊጠር ሄዱ።


ኡሪያም ንጉሡ እንዳዘዘው አደረገ።


አዋላጆቹ ግን እግዚአብሔርን በመፍራት የግብጽ ንጉሥ እንዳዘዛቸው አላደረጉም፤ ወንዶችንም ልጆች በሕይወት እንዲኖሩ ተዉአቸው።


እኔም ኤርምያስ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አልኩ፦ “በዚህች ከተማና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ይህን እናንተ የሰማችሁትን ቃል እንዳውጅ የላከኝ እግዚአብሔር ነው።


እነርሱም “እንግዲያውስ ንጉሥ ሆይ! ከይሁዳ ምርኮኞች አንዱ የሆነው ዳንኤል አንተን አያከብርህም፤ ፈርመህበት የወጣውንም ዐዋጅ በመጣስ በቀን ሦስት ጊዜ ወደ አምላኩ ይጸልያል” አሉት።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።


ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አዎ፤ እኔ ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና አንተ የሰጠኸኝን መመሪያ አልጠበቅሁም፤ ወታደሮቼን በመፍራት እነርሱ የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos