ጡት የሚጠባውን ሕፃን አንዲት ሞግዚት እንደምትታቀፈው እኔም እነርሱን ታቅፌ አንተ ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው የምታደርገኝ እነዚህን ሰዎች እኔ ፀነስኳቸውን? ወይስ እኔ ወለድኳቸውን?
1 ቆሮንቶስ 4:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ በክርስቶስ ብዙ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ወልጄአችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ በዐሥር ሺሕ የሚቈጠሩ ሞግዚቶች በክርስቶስ ቢኖሯችሁም፣ ብዙ አባቶች ግን የሏችሁም፤ በወንጌል አማካይነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወልጄአችኋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስ አእላፍ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርስቶስ ብዙ መምህራን ቢኖሩአችሁም አባቶቻችሁ ብዙዎች አይደሉም፤ እኔ በኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርት ወልጄአችኋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና። |
ጡት የሚጠባውን ሕፃን አንዲት ሞግዚት እንደምትታቀፈው እኔም እነርሱን ታቅፌ አንተ ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው የምታደርገኝ እነዚህን ሰዎች እኔ ፀነስኳቸውን? ወይስ እኔ ወለድኳቸውን?
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
አሁን ደግሞ ወንድሞች ሆይ! ያስተማርኳችሁን የወንጌል ቃል ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ፤ ይህም የወንጌል ቃል እናንተ የተቀበላችሁትና ጸንታችሁ የቆማችሁበት ነው።
እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም እኔ በጣልኩት መሠረት ላይ ይገነባል፤ ነገር ግን እያንዳንዱ በዚያ ላይ እንዴት እንደሚገነባ መጠንቀቅ አለበት።
ሌሎች ይህን ነገር ከእናንተ የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ ታዲያ፥ እኛ ከዚህ የሚበልጥ መብት እንዴት አይኖረንም? እኛ ግን በዚህ መብት አልተጠቀምንም፤ ይህን ማድረጋችንም የክርስቶስ የምሥራች ቃል ከመስፋፋት እንዳይገታ በማሰብ ሁሉን ነገር ታግሠን እንቻል ብለን ነው።
ታዲያ፥ የድካሜ ዋጋ ምንድን ነው? እንግዲህ የድካሜ ዋጋ ወንጌልን በማስተማሬ ያለኝን መብት ሳልጠቀምበት ወንጌልን የማስተማር ሥራዬን ያለ ደመወዝ በነጻ መፈጸም ነው።
እኛ የምናስተምረው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ መሆኑንና እኛም ራሳችን ስለ ኢየሱስ የእናንተ አገልጋዮች መሆናችንን ነው እንጂ ስለ ራሳችንስ አንሰብክም።
ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ።
እነሆ እኔ ጳውሎስ “ዕዳውን እከፍልሃለሁ” ብዬ በገዛ እጄ ጽፌ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሆኖም ስለ ሕይወትህ አንተ ራስህ እንኳ የእኔ ባለዕዳ መሆንክን እኔ ላስታውስህ አያስፈልግም።