Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 4:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በክርስቶስ አእላፍ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ምንም እንኳ በዐሥር ሺሕ የሚቈጠሩ ሞግዚቶች በክርስቶስ ቢኖሯችሁም፣ ብዙ አባቶች ግን የሏችሁም፤ በወንጌል አማካይነት በክርስቶስ ኢየሱስ ወልጄአችኋለሁና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ምንም እንኳ በክርስቶስ ብዙ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል ወልጄአችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በክ​ር​ስ​ቶስ ብዙ መም​ህ​ራን ቢኖ​ሩ​አ​ች​ሁም አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ሉም፤ እኔ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በት​ም​ህ​ርት ወል​ጄ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 4:15
25 Referencias Cruzadas  

ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ እስኪቀረጽ ድረስ ስለ እናንተ እንደገና ምጥ ይዞኛል።


የእግዚአብሔር ጸጋ እንደተሰጠኝ መጠን እንደ ብልኅ ግንበኛ መሠረትን ጣልኩ፤ ሌላውም በዚያ ላይ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በዚያ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።


በወንጌልም ተካፋይ እንድሆን፥ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።


እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚያበስሩ ከወንጌል ቀለባቸውን እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል።


ዳግመኛ የተወለዳችሁት በሕያውና ጸንቶ በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር እንጂ፤ ከሚጠፋ ዘር አይደለም።


ለፍጥረቱ የበኵራት እንድንሆን በገዛ ፈቃዱ በእውነት ቃል ወለደን።


እኔ ጳውሎስ “እኔ እመልሰዋለሁ፤” ብዬ በእጄ እጽፋለሁ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አላስታውስህም።


የጋራ በሆነው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከአዳኛችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይሁን።


ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት፤ ይልቁንም ጆሮዎቻቸውን የሚኮረኩራቸውን ነገር በመሻት ለራሳቸው ምኞት የሚመቹ አስተማሪዎችን የሚሰበስቡበት ጊዜ ይመጣልና።


እንግዲህ ዋጋዬ ምንድነው? በወንጌል ካለኝ መብት በሙሉ ሳልጠቀምበት ወንጌልን እየሰበክሁ ወንጌልን ያለ ክፍያ ባስተምር ነው።


ሌሎች በእናንተ ላይ ይህን የመካፈል መብት ያላቸው ከሆነ፥ እኛማ ይልቁን አይኖረንም? በዚህ መብት ግን አልተጠቀምንም፥ ነገር ግን የክርስቶስን ወንጌል በምንም እንዳንከለክል በሁሉ እንታገሣለን እንጂ።


እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስም አጠጣ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ያሳድግ ነበር፤


እንዲሁም በሌላው ሰው መሠረት ላይ አልሠራሁም፤ የክርስቶስ ስም ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን ለመስበክ ተጋሁ፤


አንተ ለአባቶቻቸው ወደ ማልህላቸው ምድር እንዳደርሳቸው፦ ‘ሞግዚት የሚጠባውን ልጅ እንደምታቅፈው እንዲሁ በብብትህ እቀፋቸው’ የምትለኝ፥ በውኑ ይህን ሕዝብ ሁሉ እኔ ፀነስሁትን? እነርሱንስ ወልጃቸዋለሁን?


ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፥ ጽድቃችንና ቅድስናችንም ቤዛችንም በተደረገልን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።


የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል።


ወንጌልን ብሰብክ እንኳ ግዴታዬ ነውና የምመካበት የለኝም፤ ወንጌልን ባልሰብክ ወዮልኝ!


ወንድሞች ሆይ! አሁን የሰበክሁላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንታችሁ የቆማችሁበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤


እኛ ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፤ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባርያዎች እናደርጋለን።


ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ፥ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆነ፤


ነገር ግን እምነት ስለ መጣ ከእንግዲህ ወዲህ በሞግዚት ሥር አይደለንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios