ነገር ግን እጁን በመለሰው ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ተወለደ፤ አዋላጂቱም ሴት “እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ልጅ ስም “ፋሬስ” ተባለ።
1 ዜና መዋዕል 4:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ዘሮች ፋሬስ፥ ሔጽሮን፥ ካርሚ፥ ሑርና ሾባል ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ዘሮች፤ ፋሬስ፣ ኤስሮም፣ ከርሚ፣ ሑር፣ ሦባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚሆር፥ ሦባል ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም ከርሚ፥ ሆርና ሱባል ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚሆር፥ ሦባል ናቸው። |
ነገር ግን እጁን በመለሰው ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ተወለደ፤ አዋላጂቱም ሴት “እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ልጅ ስም “ፋሬስ” ተባለ።
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።
የሔጽሮን ልጅ ካሌብ ዐዙባ የተባለች ሴት አግብቶ ይሪዖት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ወለደ፤ ይሪዖትም ዬሼር፥ ሾባብና አርዶን ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደች።
ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥
ከዚህ የሚከተሉትም የካሌብ ዘሮች ናቸው፦ ሑር የካሌብ ከሚስቱ ከኤፍራታ የተወለደው የመጀመሪያው ልጁ ሲሆን የሑር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ነው፤
ከዛራሕ ትውልድ አንዱ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለእግዚአብሔር ከተለየው ምርኮ በስርቆት ወስዶ በመደበቁ ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ መቅሠፍት አምጥቶ ነበር።
ነአሶን የዓሚናዳብ ልጅ፥ ዓሚናዳብ የራም ልጅ፥ ራም የአርኒ ልጅ፥ አርኒ የሔጽሮን ልጅ፥ ሔጽሮን የፋሬስ ልጅ፥ ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፥
ከፋሬስ አንሥቶ እስከ ዳዊት ያለው የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤ ፋሬስ ሔጽሮንን ወለደ፤ ሔጽሮን አራምን ወለደ፤ አራም ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።