Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 46:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የይ​ሁ​ዳም ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አው​ናን በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የፋ​ሬ​ስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስ​ሮም፥ ይሞ​ሔል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የይሁዳም ልጆች ዔር አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮችም ሐሙል።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 46:12
29 Referencias Cruzadas  

እንደገና ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች፤ “አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።


ይህን በማድረጉ እግዚአብሔርን ስላሳዘነ እግዚአብሔር እርሱንም በሞት ቀሠፈው።


እንደገናም ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ኦናን ብላ ጠራችው፤


እንደገናም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሴላ ብላ ጠራችው፤ እርሱንም የወለደችው ይሁዳ አክዚብ በሚባል ቦታ በሚኖርበት ጊዜ ነው።


ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበረ፥ እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።


የሌዊ ልጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ናቸው።


የይሳኮር ልጆች፦ ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ያሹብና ሺምሮን ናቸው።


ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


ዳዊት በኬብሮን ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች ስም እንደ ዕድሜአቸው ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦ በኲሩ የኢይዝራኤል ተወላጅ ከሆነችው ከአሒኖዓም የተወለደው አምኖን፥ ሁለተኛው የቀርሜሎስ ተወላጅ ከሆነችው ከአቢጌል የተወለደው ዳንኤል፥ ሦስተኛው የገሹር ንጉሥ የታልማይ ልጅ ከሆነችው ከማዕካ የተወለደው አቤሴሎም፥ አራተኛው ከሐጊት የተወለደው አዶንያስ፥ አምስተኛው ከአቢጣል የተወለደው ሸፋጥያ፥ ስድስተኛው ከዔግላ የተወለደው ዩትረዓም፤


የይሁዳም ዘሮች ፋሬስ፥ ሔጽሮን፥ ካርሚ፥ ሑርና ሾባል ናቸው።


ሼላ ከይሁዳ ወንዶች ልጆች አንዱ ሲሆን ዘሮቹም የሌካን ከተማ የቈረቈረው ዔር፥ የማሬሻን ከተማ የቈረቈረው ላዕዳ፥ የቤት አሽቤዓ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት የበፍታ ጨርቅ ሠሪዎች ጐሣ፥


ይሁን እንጂ ከሁሉም ይበልጥ ብርቱ የሆነና ለነገዶች ሁሉ መሪ የሚሆን ሰው የሚገኝበት የይሁዳ ነገድ ነበር፤)


ከይሁዳ ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት ስድስት መቶ ዘጠና ቤተሰቦች ነበሩ። የይሁዳ ልጅ የፋሬስ ዘሮች የዖምሪን የልጅ ልጅ የዓሚሁድን ልጅ ዑታይን መሪ አድርገው መረጡ፤ ሌሎቹ የፋሬስ ዘሮች ኢምሪና ባኒ ናቸው። የይሁዳ ልጅ የሼላ ዘሮች በኲሩ ዐሳያን እርሱም ከልጆቹ ጋር የቤተሰቡ አለቃ ነበር። የይሁዳ ልጅ የዛራሕ ዘሮች ይዑኤልን መሪያቸው እንዲሆን አደረጉ።


ከይሁዳ ነገድ የዛራ ጐሣ ተወላጅ የሆነው የመሼዛቤል ልጅ ፐታሕያ የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት ጉዳይ የፋርስ ንጉሥ እንደ ራሴ ነበር።


ነገር ግን የይሁዳን ነገድና በጣም የሚወዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ።


ከይሁዳ የዓሚናዳብ ልጅ ነአሶን


ስለ ይሁዳ ነገድም እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ የይሁዳን ነገድ ጩኸት ስማ፤ ከሌሎች ነገዶች ጋር እንዲተባበር አድርግ፤ የበረታ ኀይል ስጣቸው፤ ከጠላቶቻቸው ጋር በሚዋጉበት ጊዜ ርዳቸው።”


ጌታችን ከይሁዳ ነገድ መሆኑ የታወቀ ነው፤ ሆኖም ሙሴ ስለ ካህናት ሲናገር የይሁዳን ነገድ አስመልክቶ የተናገረው ምንም ነገር የለም።


በዚያን ጊዜ ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ከዳዊት የትውልድ ሐረግ የተነሣ አንበሳ ድል ነሥቶአል፤ እርሱ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍና ሰባቱን ማኅተሞች መክፈት ይችላል” አለኝ።


እግዚአብሔርም “የይሁዳ ነገድ ተቀዳሚ ሆኖ ይዝመት፤ እኔ ምድሪቱን ለእነርሱ አሳልፌ እሰጣለሁ” አለ።


እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት የሚሰጥህን ልጆች ይባርክልህ፤ ቤተሰብህንም ከይሁዳና ከትዕማር እንደተወለደው እንደ ፋሬስ ቤተሰብ ያድርግልህ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos