Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይሁዳ የልጁ ሚስት ከነበረችው ከትዕማር ፋሬስና ዛራሕ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የይሁዳ ልጆች በድምሩ አምስት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የልጁም ሚስት የነበረችው ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ ይሁዳም በአጠቃላይ ዐምስት ወንዶች ልጆች ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ምራ​ቱም ትዕ​ማር ፋሬ​ስ​ንና ዛራን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የይ​ሁ​ዳም ልጆች ሁሉ አም​ስት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ምራቱም ትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደችለት፤ የይሁዳም ልጆች ሁሉ አምስት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:4
14 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴላ እስከሚያድግበት ጊዜ ድረስ ሂጂና በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ኑሪ” አላት። ይህንንም ያለው እንደ ወንድሞቹ ይሞትብኛል ብሎ ስለ ሰጋ ነበር፤ ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት ተቀመጠች።


ፋሬስም ሔጽሮንና ሐሙል የተባሉ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤


የይሁዳም ዘሮች ፋሬስ፥ ሔጽሮን፥ ካርሚ፥ ሑርና ሾባል ናቸው።


ከይሁዳ ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት ስድስት መቶ ዘጠና ቤተሰቦች ነበሩ። የይሁዳ ልጅ የፋሬስ ዘሮች የዖምሪን የልጅ ልጅ የዓሚሁድን ልጅ ዑታይን መሪ አድርገው መረጡ፤ ሌሎቹ የፋሬስ ዘሮች ኢምሪና ባኒ ናቸው። የይሁዳ ልጅ የሼላ ዘሮች በኲሩ ዐሳያን እርሱም ከልጆቹ ጋር የቤተሰቡ አለቃ ነበር። የይሁዳ ልጅ የዛራሕ ዘሮች ይዑኤልን መሪያቸው እንዲሆን አደረጉ።


ከይሁዳ ነገድ የዛራ ጐሣ ተወላጅ የሆነው የመሼዛቤል ልጅ ፐታሕያ የእስራኤልን ሕዝብ በሚመለከት ጉዳይ የፋርስ ንጉሥ እንደ ራሴ ነበር።


የይሁዳ ነገድ አባላት፦ የዘካርያስ የልጅ ልጅ የሆነው የዑዚያ ልጅ ዐታያ፤ ሌሎች የቀድሞ አያቶቹ የይሁዳ ልጅ የሆነው የፋሬስ ዘሮች የሆኑትን አማርያን፥ ሸፋጥያንና ማሀላልኤልን ይጨምራሉ።


ዛራ፥ ሳኡልና የእነርሱ ተወላጆች ናቸው።


ይሁዳ ፋሬስንና ዛራን ትዕማር ከምትባል ሴት ወለደ፤ ፋሬስ ሔስሮንን ወለደ፤ ሔስሮንም አራምን ወለደ፤


ነአሶን የዓሚናዳብ ልጅ፥ ዓሚናዳብ የራም ልጅ፥ ራም የአርኒ ልጅ፥ አርኒ የሔጽሮን ልጅ፥ ሔጽሮን የፋሬስ ልጅ፥ ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፥


እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት የሚሰጥህን ልጆች ይባርክልህ፤ ቤተሰብህንም ከይሁዳና ከትዕማር እንደተወለደው እንደ ፋሬስ ቤተሰብ ያድርግልህ።”


ከፋሬስ አንሥቶ እስከ ዳዊት ያለው የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤ ፋሬስ ሔጽሮንን ወለደ፤ ሔጽሮን አራምን ወለደ፤ አራም ዐሚናዳብን ወለደ፤ ዐሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ ሰልሞን ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ እሴይም ዳዊትን ወለደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos