Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ዜና መዋዕል 4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


የይሁዳ ትውልድ

1 የይሁዳ ልጆች ፋሬስ፥ ኤስሮም፥ ከርሚሆር፥ ሦባል ናቸው።

2 የሦባልም ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤትም አሑማይንና ላሃድን ወለደ። እነዚህ የጾርዓውያን ወገኖች ናቸው።

3 እነዚህም የኤጣም አባት ልጆች ናቸው፤ ኢይዝራኤል፥ ይሽማ፥ ይድባሽ፥ እኅታቸውም ሃጽሌልፎኒ ትበባል ነበር።

4 የጌዶርም አባት ፋኑኤል፥ የሑሻም አባት ኤጽር ነበር፤ እነዚህ የቤተልሔም አባት የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጆች ናቸው።

5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።

6 ነዕራም አሑዛምን፥ ኦፌርን፥ ቴምኒን፥ አሐሽታሪን ወለደችለት። እነዚህ የነዕራ ልጆች ናቸው።

7 የሔላም ልጆች ዴሬት፥ ይጽሐር፥ ኤትናን ናቸው።

8 ቆጽ ዓኑብን፥ ጾቤባን፥ የሃሩምንም ልጅ የአሐርሔልን ወገኖች ወለደ።

9 ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም፦ “በጣር ወልጄዋለሁና” ብላ ስሙን፦ ያቤጽ ብላ ጠራችው።

10 ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።

11 የሹሐም ወንድም ክሉብ የኤሽቶንን አባት ምሒርን ወለደ።

12 ኤሽቶንም ቤትራ-ፋንና ፋሴሐን የዒርናሐሽንም አባት ተሒናን ወለደ፤ እነዚህ የሬካ ሰዎች ናቸው።

13 የቄኔዝም ልጆች ጎቶንያልና ሠራያ ነበሩ። የጎቶንያልም ልጅ ሐታት ነበረ።

14 መዖኖታይ ዖፍራን ወለደ። ሠራያም የጌ-ሃራሽምን አባት ኢዮአብን ወለደ፤ እነርሱም ጠራቢዎች ነበሩ።

15 የዮፎኒም ልጅ ካሌብ ልጆች ዒሩ፥ ኤላ፥ ነዓም ነበሩ፤ የኤላም ልጅ ቄኔዝ ነበረ።

16 የይሃሌልኤል ልጆች ዚፍ፥ ዚፋ፥ ቲርያ፥ አሣርኤል ነበሩ።

17 የዕዝራም ልጆች ዬቴር፥ ሜሬድ፥ ዔፌር፥ ያሎን ነበሩ፤ የሜሬድም ሚስት ማርያምን፥ ሸማይን፥ የኤሽትምዓን አባት ይሽባን ወለደች።

18 አይሁዳዊቱም ሚስቱ የጌዶርን አባት ዬሬድን፥ የሦኮንም አባት ሔቤርን፥ የዛኖዋንም አባት ይቁቲኤልን ወለደች። እነዚህም ሜሬድ ያገባት የፈርዖን ልጅ የቢትያ ልጆች ናቸው።

19 የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ልጆች የገርሚው የቅዒላ አባትና ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ ነበሩ።

20 የሺሞንም ልጆች አምኖን፥ ሪና፥ ቤን-ሐናን፥ ቲሎን ነበሩ። የይሽዒም ልጆች ዞሔትና ቢን-ዞሔት ነበሩ።

21 የይሁዳም ልጅ የሴሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአሽቤዓ-ቤት የሚሆኑ ጥሩ በፍታ የሚሠሩ ወገኖች፥

22 ዮቂም፥ የኮዜባ ሰዎች፥ ኢዮአስ፥ ሞዓብን የገዛ ሣራፍ፥ ያሹቢሌሔም ነበሩ። ይህ መዝገብ ጥንታዊ ነው።

23 እነዚህ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠራተኞች ነበሩ። በዚያ የንጉሡን ሥራ ለመሥራት በእርሱ ዘንድ ይቀመጡ ነበር።


የስምዖን ትውልድ

24 የስምዖንም ልጆች፤ ነሙኤል፥ ያሚን፥ ያሪን፥ ዛራ፥ ሳኡል ነበሩ፤

25 እንዲሁም ልጁ ሰሎም፥ ልጁ ሚብሣም፥ ልጁ ሚሽማዕ ነበሩ።

26 የሚሽማዕም ልጆች፤ ልጁ ሃሙኤል፥ ልጁ ዘኩር፥ ልጁ ሰሜኢ ነበሩ።

27 ለሰሜኢም ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ለወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሩአቸውም፥ ወገናቸውም ሁሉ እንደ ይሁዳ ልጆች አልተባዙም።

28 እነርሱ የሰፈሩት በቤር-ሳቤህ፥ በሞላዳ፥ በሐጸርሹዓል፥

29 በቢልሃ፥ በዔጼም፥ በቶላድ፥

30 በቤቱኤል፥ በሔርማ፥ በጺቅላግ፥

31 በቤት-ማርካቦት፥ በሐጸር-ሱሲም፥ በቤት-ቢሪ፥ በሸዓራይም ነበር። እስከ ዳዊትም መንግሥት ድረስ ከተሞቻቸው እነዚህ ነበሩ።

32 መንደሮቻቸው ኤጣም፥ ዐይን፥ ሬሞን፥ ቶኬን፥ ዓሻን፥ አምስቱ ከተሞች ነበሩ፤

33 እስከ በኣልም ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ የነበሩ መንደሮቻቸው ሁሉ ነበሩ። መቀመጫቸውና የትውልዳቸው መዝገቦች እነዚህ ናቸው።

34 ምሾባብ፥ የምሌክ፥ የአሜስያስ ልጅ ኢዮስያ፥

35 ኢዮኤል፥ የዮሺብያ ልጅ፥ የሠራያ ልጅ የዓሢኤል ልጅ ኢዩ፥

36 ኤልዮዔናይ፥ ያዕቆባ፥ የሾሐያ፥ ዓሣያ፥ ዓዲዔል፥ ዩሲምኤል፥ በናያስ፥

37 የሺፊ ልጅ ዚዛ፥ የአሎን ልጅ የይዳያ ልጅ የሺምሪ ልጅ የሸማያ ልጅ፤

38 እነዚህ በስማቸው የተጠሩ በወገኖቻቸው ላይ አለቆች ነበሩ፤ የአባቶቻቸውም ቤቶች እጅግ በዝተው ነበር።

39 ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ለመፈለግ ወደ ጌዶር መግቢያ እስከ ሸለቆው ምሥራቅ ድረስ ሄዱ።

40 የለመለመም እጅግም ያማረ መሰማሪያ አገኙ፥ ምድሪቱም ሰፊ ጸጥታም ያለላትና ሰላም የሰፈነባት ነበረች፤ በቀድሞም ጊዜ በዚያ ተቀምጠው የነበሩ ከካም ወገን ነበሩ።

41 እነዚህም በስማቸው የተጻፉ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን መጥተው ድንኳኖቻቸውንና በዚያ የተገኙትን ምዑናውያንን መቱ፥ እስከ ዛሬም ድረስ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ በዚያም ለመንጎቻቸው መሰማሪያ ነበረና በስፍራቸው ተቀመጡ።

42 የስምዖንም ልጆች አምስት መቶ ሰዎች ወደ ሴይር ተራራ ሄዱ፤ አለቆቻቸውም የይሽዒ ልጆች፥ ፈላጥያ፥ ነዓርያ፥ ረፋያ፥ ዑዝኤል ነበሩ።

43 ያመለጡትንም የአማሌቃውያንን ትሩፋን መቱ፥ በዚያም እስከ ዛሬ ድረስ ተቀምጠዋል።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos