Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዛራሕ ትውልድ አንዱ የሆነው የካርሚ ልጅ ዓካን ለእግዚአብሔር ከተለየው ምርኮ በስርቆት ወስዶ በመደበቁ ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ መቅሠፍት አምጥቶ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የከርሚ ወንድ ልጅ አካን፤ እርሱም ዕርም የሆነ ነገር ሰርቆ በእስራኤል ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደረገ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የዘ​ም​ሪም ልጅ ከርሚ ነው፤ የከ​ር​ሚም ልጅ እስ​ራ​ኤ​ልን ያስ​ጨ​ነቀ፥ እር​ሙን ሰርቆ የበ​ደለ አካን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:7
10 Referencias Cruzadas  

የእርሱም ወንድም ዛራሕ አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ዚምሪ፥ ኤታን፥ ሄማን፥ ካልኮልና ዳርዳዕ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤


ኤታንም ዐዛርያ የተባለ አንድ ወንድ ልጅ ወለደ።


የይሁዳም ዘሮች ፋሬስ፥ ሔጽሮን፥ ካርሚ፥ ሑርና ሾባል ናቸው።


እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል።


እነዚህንም የረከሱ ጣዖቶች ወደ ቤትህ አታስገባ፤ ብታስገባ ግን አንተም እንደ እነርሱ ትጠፋለህ፤ እነርሱ ለጥፋት የተገቡ ስለ ሆነ በጣም ልትጠላቸውና ልትጸየፋቸው ይገባል።


የዛራ ልጅ ዓካን መደምሰስ በሚገባቸው ነገሮች እምነተቢስ ሆኖ ትእዛዝ በማፍረሱ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ላይ አልወረደምን? በጥፋቱም የጠፋው እርሱ ብቻ አልነበረም።’ ”


እናንተ ግን በእስራኤል ሰፈር ችግርንና ጥፋትን እንዳታስከትሉ መደምሰስ ከሚገባቸው ነገሮች ማናቸውንም ጓጒታችሁ ከመውሰድ ራሳችሁን ጠብቁ፤


ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos