Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 38:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ነገር ግን እጁን በመለሰው ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ተወለደ፤ አዋላጂቱም ሴት “እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ልጅ ስም “ፋሬስ” ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ነገር ግን እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ!” አለች፤ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እጁን በመ​ለሰ ጊዜ እነሆ፥ ወን​ድሙ ወጣ፤ እር​ስ​ዋም፥ “ለምን ጥሰህ ወጣህ? ስትል ስሙን ፋሬስ” ብላ ጠራ​ችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እንዲህም ሆነ እጁን በመለሰ ጊዜ እነሆ ወንድሙ ወጣ፤ እርስዋም፦ ለምን ጥስህ ወጣህ? አለች፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 38:29
10 Referencias Cruzadas  

በምትወልድበትም ጊዜ ከመንትያዎቹ አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ሴት ቀይ ክር በእጁ ላይ አሰረችለትና “ይህ በመጀመሪያ ወጣ” አለች።


የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።


ይሁዳ የልጁ ሚስት ከነበረችው ከትዕማር ፋሬስና ዛራሕ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። የይሁዳ ልጆች በድምሩ አምስት ነበሩ።


ከይሁዳ ነገድ በኢየሩሳሌም ለመኖር የሄዱት ስድስት መቶ ዘጠና ቤተሰቦች ነበሩ። የይሁዳ ልጅ የፋሬስ ዘሮች የዖምሪን የልጅ ልጅ የዓሚሁድን ልጅ ዑታይን መሪ አድርገው መረጡ፤ ሌሎቹ የፋሬስ ዘሮች ኢምሪና ባኒ ናቸው። የይሁዳ ልጅ የሼላ ዘሮች በኲሩ ዐሳያን እርሱም ከልጆቹ ጋር የቤተሰቡ አለቃ ነበር። የይሁዳ ልጅ የዛራሕ ዘሮች ይዑኤልን መሪያቸው እንዲሆን አደረጉ።


የይሁዳ ነገድ አባላት፦ የዘካርያስ የልጅ ልጅ የሆነው የዑዚያ ልጅ ዐታያ፤ ሌሎች የቀድሞ አያቶቹ የይሁዳ ልጅ የሆነው የፋሬስ ዘሮች የሆኑትን አማርያን፥ ሸፋጥያንና ማሀላልኤልን ይጨምራሉ።


ከፋሬስ ዘሮች መካከል በጀግንነታቸው ታዋቂዎች የሆኑ 468 ሰዎች በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆኑ።


የቀሩት የይሁዳ ልጆች ሴሎም ፋሬስ ዛራና ተወላጆቻቸው ናቸው።


ይሁዳ ፋሬስንና ዛራን ትዕማር ከምትባል ሴት ወለደ፤ ፋሬስ ሔስሮንን ወለደ፤ ሔስሮንም አራምን ወለደ፤


ነአሶን የዓሚናዳብ ልጅ፥ ዓሚናዳብ የራም ልጅ፥ ራም የአርኒ ልጅ፥ አርኒ የሔጽሮን ልጅ፥ ሔጽሮን የፋሬስ ልጅ፥ ፋሬስ የይሁዳ ልጅ፥ ይሁዳ የያዕቆብ ልጅ፥


እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት የሚሰጥህን ልጆች ይባርክልህ፤ ቤተሰብህንም ከይሁዳና ከትዕማር እንደተወለደው እንደ ፋሬስ ቤተሰብ ያድርግልህ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos