“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
ምሳሌ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤ እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔርን መሪ አድርገው፤ እርሱም በትክክለኛው መንገድ ይመራሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች። |
“አንተም፥ ልጄ ሰሎሞን ሆይ! እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም አምልከው፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይጥልሃል።
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባርያህን ጸሎት፥ ስምህን በመፍራት የሚደሰቱትን የባርያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬ ለባርያህ እባክህን አከናውንለት፥ በዚህም ሰው ፊት ሞገስን ስጠው። እኔም የንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
አምላኬም መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና ሕዝቡን ሰብስቤ እንድቆጥራቸው በልቤ አስቀመጠ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ።
እኔ በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ፤ እርሱ ከተማዬን ይሠራል፥ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
አንዳንድ ጊዜ ደመናው ለጥቂት ቀኖች በማደሪያው ላይ ይቈይ ነበር፤ በዚያ ጊዜ እንደ ጌታ ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፤ እንደ ጌታም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።
ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።