ናሆም 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኃይልዋ ነበሩ፤ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወሰን የሌለው ኀይልዋ ከግብጽ ከራስዋና ከኢትዮጵያ ይመጣ ነበር፤ የፉጥና ሊብያ ሰዎችም ተባባሪዎችዋ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ፣ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ። |
እርሱም ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ይዞ ነበር። ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም፤ እነርሱም የልብያ ሰዎች ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።
ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? በጌታ ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው፥