በከተሞቻቸው ሁሉና በኢየሩሳሌምም፦ “እንደተጻፈው ዳሶችን ለመስራት ወደ ተራራ ውጡ፥ የዘይትና የበረሀ ወይራ፥ የባርሰነት፥ የዘንባባና የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ” ብለው ይናገሩና ያውጁ።
ዘሌዋውያን 23:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነዚህ የጌታ በዓላት፥ ለእነርሱ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጁአቸው፥ የተቀደሱ ጉባኤዎች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የተመረጡ የእግዚአብሔር በዓላት ብላችሁ በተወሰኑላቸው ጊዜያት የምታውጇቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እነዚህ ናቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእያንዳንዳቸው በተወሰነላቸው ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት እየተሰበሰባችሁ የምታከብሩአቸው ዋና ዋናዎቹ በዓላት እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የእግዚአብሔር በዓላት፥ በየዘመናቸው የምታውጁአቸው፥ የተቀደሱ ጉባኤያት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የእግዚአብሔር በዓላት፥ በየዘመናቸው የምታውጁአቸው፥ የተቀደሰ ጉባኤ ናቸው። |
በከተሞቻቸው ሁሉና በኢየሩሳሌምም፦ “እንደተጻፈው ዳሶችን ለመስራት ወደ ተራራ ውጡ፥ የዘይትና የበረሀ ወይራ፥ የባርሰነት፥ የዘንባባና የለመለመውን ዛፍ ቅርንጫፍ አምጡ” ብለው ይናገሩና ያውጁ።
በዚያም ቀን ታውጃላችሁ፤ የተቀደሰ ጉባኤም ታደርጋላችሁ። የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። በምትቀመጡበት አገር ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።
“የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉንም ቁርባን፥ መሥዋዕቱንም፥ የመጠጡንም ቁርባን፥ ለጌታም በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን፥ እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው ቀናቸው እንድታቀርቡባቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እንዲሆኑ የምታውጁአቸው የጌታ በዓላት እነዚህ ናቸው።