ዘሌዋውያን 11:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእነዚህንም በድን የሚያነሣ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሁን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ማታም ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም በድን የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። |
ሰኮናውም የተከፈለ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ያልተሰነጠቀ፥ የሚያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ እርሱንም የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል።
ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
በሰባተኛውም ቀን ካህኑ ዳግም ያየዋል፤ እነሆም፥ ደዌው ቢከስም፥ ደዌውም በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ እከክ ነው፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል።
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ጠጉሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
“ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው ከፈሳሹ ነገር ሲነጻ፥ ስለ መንጻቱ ሰባት ቀን ይቈጥራል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ ገላውንም በምንጭ ውኃ ይታጠባል፥ እርሱም ንጹሕ ይሆናል።
ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።
የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
የጊደሪቱንም አመድ የሰበሰበው ሰው ልብሱን ያጥባል እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ይህም ለእስራኤል ልጆች በመካከላቸውም ለሚኖር መጻተኛ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
ንጹሑም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ርኩስ በሆነው ሰው ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ያነጻዋል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በመሸም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።
ነገር ግን ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ የመንጻት ሥርዓቶች የሚውሉ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ስለ ሆኑ፥ እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ ናቸው።
ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።