ዘሌዋውያን 17:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የሞተውን ወይም አውሬ የገደለውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገሩ ተወላጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 “ ‘ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን የበላ ማንኛውም የአገር ተወላጅ ወይም መጻተኛ ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ በሥርዐቱ መሠረት እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም የውጪ አገር ተወላጅ የሆነ ሰው፥ ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ ቢበላ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የሀገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፤ በውኃም ይታጠባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የሞተውን ወይም አውሬ የሰበረውን የሚበላ ሰው ሁሉ፥ የአገር ልጅ ወይም እንግዳ ቢሆን፥ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል። Ver Capítulo |