Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 11:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ማንም ሰው ከበድኑ ቢበላ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ማንም ከዚህ እንስሳ ማንኛውንም ክፍል ቢበላ ልብሱን ይጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን፤ ማንም ሰው የዚያን እንስሳ በድን ቢሸከም ልብሱን ይጠብ፤ እርሱም እስከ ምሽት ድረስ ርኩስ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ከበ​ድ​ኑም የሚ​በላ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ በድ​ኑ​ንም የሚ​ያ​ነሣ፤ ልብ​ሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ይሆናል፤ በድኑንም የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 11:40
25 Referencias Cruzadas  

ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


እኔም እንዲህ አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወይኔ! እነሆ፥ ሰውነቴ አልረከሰችም፥ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ፥ የሞተ ወይም እንስሳ የገደለውን ከቶ አልበላሁም፥ ርኩስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አልገባም።


ካህናቱ የሞተ ወይም ሌላ አውሬ የገደለውን ወፍ ወይም እንስሳ አይብሉ።


በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።


“ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


በተዘጋበትም ጊዜ ሁሉ ወደ ቤቱ የሚገባ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባቸዋል፤ ካህኑም በጌታ ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ያስተሰርይለታል።


እነዚህንም ነገሮች የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ልብሱንም ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።


ወደ ዐዛዜል የሄደውን ፍየል የወሰደው ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ይገባል።


ያቃጠላቸውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል።


እንዲህ ያሉትን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ።


በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የገደለውን አይብላ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይፈልቃል።


ንጹሑም ሰው በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ርኩስ በሆነው ሰው ላይ ይረጨዋል፤ በሰባተኛውም ቀን ያነጻዋል፤ እርሱም ልብሱን ያጥባል፥ ገላውንም በውኃ ይታጠባል፥ በመሸም ጊዜ ንጹሕ ይሆናል።


የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።


ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።


“አንተ ግን ለጌታ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ እንዲበላ ልትሰጠው ትችላለህ፤ ወይም ለውጭ አገር ሰው ልትሸጠው ትችላለህ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos